የሀገር ውስጥ ዜና

ተጨማሪ 573 ሰዎች ኮሮና ቫይረስ ሲገኝባቸው የ4 ሰዎች ህይወት አልፏል

By Tibebu Kebede

January 03, 2021

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 25፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ባለፉት 24 ሰዓታት ለ6 ሺህ 387 ሰዎች የላቦራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 573 ሰዎች ኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።

ባለፉት 24 ሰዓታት በኮሮናቫይረስ ሳቢያ የ4 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ በአጠቃላይ በቫይረሱ ለህልፈት የተዳረጉ ሰዎች ቁጥር 1 ሺህ 948 ደርሷል።

በኢትዮጵያ በአጠቃላይ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 125 ሺህ 622 መድረሱንም ሚኒስቴሩ አስታውቋል።

በትናንትናው ዕለት 42 ሰዎች ከቫይረሱ ማገገማቸውን ተከትሎ በአጠቃላይ ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 112 ሺህ 367 ሆኗል።

በአሁኑ ወቅት ቫይረሱ ካለባቸው 11 ሺህ 305 ሰዎች መካከል 239 ያህሉ በጽኑ ሕክምና ላይ መሆናቸው ተገልጿል።

በአገሪቱ እስካዛሬ ድረስ በአጠቃላይ ለ1 ሚሊየን 817 ሺህ 965 ሰዎች የኮሮናቫይረስ ምርመራ ተደርጓል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤ ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!