የሀገር ውስጥ ዜና

የጋምቤላ እና የኦሮሚያ ክልሎች የሰላም እና የልማት ኮንፍረንስ እየተካሄደ ነው

By Tibebu Kebede

January 04, 2021

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 26 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የጋምቤላ እና የኦሮሚያ አጎራባች ክልሎች የሰላም እና የልማት ኮንፍረንስ በጋምቤላ ከተማ እየተካሄደ ነው።

በውይይቱ ላይ የሁለቱ ክልሎች የሰላም እና የጸጥታ ቢሮ ኃላፊዎች፣ የዞን መስተዳድሮች እና የጸጥታ ቢሮ ኃላፊዎች እንዲሁም ሌሎች ተጋባዥ እንግዶች ተገኝተዋል።

የጋምቤላ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኡሞድ ኡጁሉ በሁለቱ ህዝቦች መካከል ለዘመናት የቆየውን የእርስ በእርስ ግንኙነት በማጠናከር ወደ ተሻለ ደረጃ ማድረስ እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል።

መድረኩ በሁለቱ ህዝቦች መካከል ያለውን የመቻቻል፣ የሰላም እና የአብሮነት እሴት ለማስቀጠል ያለመ መሆኑን ኢብኮ ዘግቧል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤ ተንቀሳ የፋና ድረ ቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!