Fana: At a Speed of Life!

የደቡብ ክልል አመራሮች ቡድን በምዕራብ ኦሞ ዞን የደረሰውን የእሳት ቃጠሎና በቃጠሎው ምክንያት የተፈናቀሉ ዜጎችን ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 26፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)የደቡብ ክልል አመራሮች ቡድን በምዕራብ ኦሞ ዞን ቤራ ወረዳ ሾላ ቀበሌ የደረሰውን የእሳት ቃጠሎና በቃጠሎው ምክንያት የተፈናቀሉ የህብረተሰብ ክፍሎችን ጎብኝተዋል።

ባለፈው በታህሳስ 19 በዞኑ ቤሮ ወረዳ ሾላ ከተማ የተከሰተው ከባድ ቃጠሎ ከፍተኛ ውድመት ማድረሱ ይታወሳል።

በቃጠሎው ምክንያት ምንም እንኳን በሰው ህይወት ላይ ጉዳት ባይደርስም ከፍተኛ የንብረት ውድመት ማድረሱ ተነግሯል ።

የደቡብ ክልል የከፍተኛ አመራሮች ቡድንና የዞንና ወረዳ የስራ ሃላፊዎች የጉዳቱን መጠንና ተፈናቃዮች ያሉበትን ሁኔታ ተዘዋውሮ የጎበኘ ሲሆን፥ ከተወካዮች ጋርም ውይይት አካሂዷል።

በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የግብርና ክላስተር አስተባባሪ በሆኑት በአቶ አንተነህ ፈቃዱ የተመራው የክልል፣የዞንና የወረዳ አመራሮች ቡድን የጉዳቱን መጠንና ጉዳተኞቹ ያሉበትን ሁኔታ ተመልክተዋል።

ለተፈናቃዮች ሰብዓዊ ድጋፍ ለማቅረብና ህብረተሰቡን በዘላቂነት ለማቋቋም እንደሚሰራ በየደረጃው የተወከሉ አመራሮች አስታውቀዋል ።

በአካባቢው የፋይናንስ ተቋማትና የመንገድ መሰረተ ልማት አለመኖር ጉዳቱን የከፋ እንዳደረገው ተጎጅዎቹ ማንሳታቸውን ከደቡብ ክልል መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል ።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C (https://www.fanabc.com/)
Front page – Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.