Fana: At a Speed of Life!

ኤጀንሲው ከሃይማኖት ተቋማት እና ከኢትዮጵያ ሚድዋይፍስ ማህበር ጋር የወሳኝ ኩነት ምዝገባ ስራን ለማጠናከር የሚረዳ የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረመ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 26፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢሚግሬሽን ዜግነትና ወሳኝ ኩነት ኤጀንሲ ከሃይማኖት ተቋማት እና ከኢትዮጵያ ሚድዋይፍስ ማህበር ጋር የወሳኝ ኩነት ምዝገባ ስራን ለማጠናከር የሚረዳ የጋራ መግባቢያ ሰነድ ተፈራርሟል፡፡

የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ ሙጂብ ጀማል የወሳኝ ኩነት ምዝገባ ስራ ከጊዜ ወደጊዜ እየተሻሻለ ቢመጣም ከሌሎች የአፍሪካ ሃገራት ጋር ሲነፃፀር ያለበት ደረጃ ዝቅተኛ ነው ብለዋል፡፡

ስለሆነም ይህን ለማሻሻል ኤጀንሲው ከሚያከናውናቸው ተግባራት አንዱ በወሳኝ ኩነት ምዝገባ ስራ ላይ ከፍተኛ ሚና ያላቸው መንግስታዊ እና መንግስታዊ ካልሆኑ ተቋማት ጋር የጋራ መግባቢያ ሰነዶችን በመፈራረም በግንዛቤ ማስጨበጫ ስራ እንዲሁም የምዝገባ ስራውን በማሳደግ ዙሪያ ላይ የተለያዩ ተግባራትን ማከናወን እንደሆነ ገልፀዋል፡፡

በጋራ ስምምነት ሰነድ ፊርማ ስነ-ስርአቱ ላይ የተገኙት የሃይማኖት አባቶችም ሁሉም የሃይማኖት ተቋማት ቀደም ሲል ጀምሮ የወሳኝ ኩነት ምዝገባ ስራ ላይ ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንደነበራቸው እና በሁሉም ሃይማኖቶች የሚደገፍ ተግባር መሆኑን ገልፀዋል፡፡

በየደረጃው ያሉ የሃይማኖት መሪዎች የሃይማኖት ተከታዮቻቸውን በማስገንዘብ እና ህብረተሰቡ የሚገጥመውን የልደት፣ የጋብቻ፣ የፍቺ እንዲሁም የሞት ኩነት በማስመዝገብ የበኩሉን እንዲወጣ ማሳሰባቸውን ከኢሚግሬሽን ዜግነትና ወሳኝ ኩነት ኤጀንሲ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.