Fana: At a Speed of Life!

የተሰነደው 23 ነጥብ 8 ቢሊየን ወደ ገንዘብ እንዲቀየር ኮሚቴው አሳሰበ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 26፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) የከፍተኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት በሰነድ ብቻ ያስቀመጠው 23 ነጥብ 8 ቢሊየን ብር፤ ወደ ገንዘብ እንዲቀየር የገቢ፣ በጀት እና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አሳሰበ፡፡

ቋሚ ኮሚቴው የቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤቱን የሥራ እንቅስቃሴ በአካል ከጎበኘ በኋላ ግብረ-መልስ ሰጥቷል፡፡

የቋሚ ኮሚቴው የመስክ ምልከታ ቡድን አስተባባሪ አቶ መስፍን መሸሻ ግብረ-መልሱን ባቀረቡበት ወቅት የሚሠሩ እና የማይሠሩ የግዢ እና የሽያጭ መመዝገቢያ ማሽኖች ተለይተው፤ ጥገና፣ ዕድሳት እና ክትትል እንዲደረግላቸው ጠቁመዋል፡፡

የታክስ ማጭበርበርን እና ስወራን በሚመለከትም ክትትል እና ቁጥጥር እንዲደረግ እና ግብር የማያሳውቁ እና የሚያሳንሱ ግብር ከፋዮችን መቆጣጠሩ ተጠናክሮ እንዲቀጥል አሳስበዋል፡፡

በሰነድ የተቀመጠው 23 ነጥብ 8 ቢሊየን ብርም ወደ ገንዘብ እንዲቀየር ከፍተኛ ክትትል እንዲደረግም በቋሚ ኮሚቴው ስም መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

በሌላ በኩልም ከተጨማሪ ዕሴት ታክስ ማሳወቅ ጋር በተያያዘ 52 ድርጅቶች ያላሳወቁ መሆናቸው፣ 496 የሽያጭ መመዝገቢያ ማሽኖች በሥራ ላይ አለመሆናቸው እና 199ኙ ወደ ሥራ የማይመለሱ መሆናቸውን በቅርንጫፉ የአሠራር ክፍተትነት ተነስተዋል፡፡

የሽያጭ እና የግዢ መረጃዎችን በመረጃ መረብ የመላክ ስልጠና እና መረጃን ወደ ኮምፒውተር ሥርዓት የመቀየር ተግባር እንዲሁም ለሕጻናት ማቆያ ዝግጅት ትኩረት አለመሰጠቱ በዕጥረት ተጠቅሰዋል፡፡

ኮሚቴው 87 ነጥብ 5 በመቶ ግብር ከፋይ በኢ-ታክስ ማወቁ እና የውዝፍ ዕዳ አሰባሰብ ከዕቅድ አኳያ የተበሻለ መሆኑ ተነስቷል፡፡

የታክስ ኦዲትን በሚመለከትም የተሻለ አፈጻጸም መኖሩ፣ እንዲሁም የግዢ ተግባር በዕቅድ መመራቱ፣ አዋጆች እና ሕጎች ተደራሽ እንዲሆኑ መደረጋቸውን አበረታቷል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.