Fana: At a Speed of Life!

በእንግሊዝ አዲስ የእንቅስቃሴ ገደብ ይፋ ሆነ

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 26 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የእንግሊዙ ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን ከአዲሱ የኮሮና ቫይረስ ስርጭት ጋር በተያያዘ አዲስ የእንቅስቃሴ ገደብ ይፋ አደረጉ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይፋ ያደረጉት የእንቅስቃሴ ገደብ በመላ ሃገሪቱ የሚተገበር ነው ተብሏል።

ይህን ተከትሎም ሰዎች በጣም አስፈላጊ ከሆኑ ጉዳዮች ውጭ ከቤት መውጣት አይፈቀድላቸውም።

ከዚህ ጋር ተያይዞም ስራቸውን ቤታቸው ሆነው እንዲሰሩና ትምህርት ቤቶችም ተዘግተው እንዲቆዩ ይደረጋልም ነው የተባለው።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ቤቴሌቪዥን ባስተላለፉት መልዕክት ህዝቡ ህግና ደንቦችን እንዲከተል አጽንኦት ሰጥተዋል።

በመልዕክታቸው መጭዎቹ ሳምንታት ፈታኝ ይሆናሉ ብለዋል።

ከእንግሊዝ በተጨማሪም ስኮትላንድ ቀደም ብላ በቤት ይቆዩ መመሪያ ያወጣች ሲሆን ትምህርት ቤቶችም እንዲዘጉ ወስናለች።

በሰሜን አየርላንድ ደግሞ ከአዲሱ የኮሮና ቫይረስ ስርጭት ጋር በተያያዘ አዳዲስ መመሪያዎችን ይፋ ማድረግ በሚቻልበት አግባብ ላይ ለመምከር የመንግስት የስራ ሃላፊዎች ስብሰባ ተቀምጠዋል።

በእንግሊዝ ከአዲሱ የፈረንጆች አመት ወዲህ በሆስፒታል የሚገኙና የኮሮና ቫይረስ ያለባቸው ሰዎች ቁጥር በ50 በመቶ መጨመሩ ይነገራል።

ከዚህ ጋር ተያይዞም አብዛኛዎቹ የሆስፒታል አልጋዎች በኮሮና ቫይረስ ታማሚዎች የተያዙ መሆናቸው ነው የተነገረው።

በሃገሪቱ ለተከታታይ ቀናት ከ50 ሺህ በላይ አዳዲስ ሰዎች በየቀኑ በቫይረሱ እየተያዙ ነው።

ምንጭ፦ ቢቢሲ

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.