ዓለምአቀፋዊ ዜና

ኢትዮጵያ፣ ኬንያና ሶማሊያ በጁባላንድ ኮሪደር በጋራ መስራት በሚቻልበት አግባብ ላይ ተወያዩ

By Tibebu Kebede

January 05, 2021

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 27 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ፣ ኬንያና ሶማሊያ በሚዋሰኑበት ድንበር በጁባላንድ ኮሪደር በጋራ መስራት በሚቻልበት አግባብ ላይ ተወያዩ፡፡

በውይይቱ በቀጠናው ስላለው ወቅታዊ የጠላት እንቅስቃሴ የመከሩ ሲሆን በቀጠናው በጋራ ለመስራት መግባባት ላይ ደርሰዋል፡፡

በውይይቱ ላይ የሴክተር ሁለት አዛዥ ብርጋዴር ጄኔራል ጄማ፣ የሴክተር ስድስት ምክትል አዛዥ ኮሎኔል ማኩርጋ ፓናርድ፣ የ5ኛ ሞተራይዝድ ዋና አዛዥ ኮሎኔል አሰፋ መኮንን፣ የጁባላንድ ክልል ከፍተኛ የጦር መኮንኖችና የፌደራል ኤስ ኤን ኤ ከፍተኛ አመራሮች እንዲሁም የጁባላንድ የፀጥታ ዘርፍ ሃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡

የጁባ ላንድ ምክትል ፕሬዚዳንት ማህሙድ ሰይድ ሶማሊያ ፣ ኢትዮጵያና ኬንያ ወንድማማች ህዝቦች መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡

የአዋሳኝ ድንበር ቦታዎች ላይ ሰላምና መረጋጋት እንዲኖር የጋራ ጠላት የሆነውን አልሸባብን በጋራ መዋጋት ይገባልም ብለዋል፡፡

በሶማሊያ የአፍሪካ ህብረት ሰላም አስከባሪ ሃይል (አሚሶም) የሴክተር ስድስት ምክትል አዛዥ ኮሎኔል ማኩርጋ ፓናርድ፥ የኢትዮጵያና ኬንያ ሰላም አስከባሪ ሃይል በጋራ በአካባቢው ሰላም ለማስፈን እየሰሩ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

የክልሉ የፀጥታ ሃይል፣ ከፍተኛ የስራ አመራሮችና ህብረተሰቡም ከጎናቸው እንደሆነ መናገራቸውን ከመከላከያ ሰራዊት ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

የ5ኛ ሞተራይዝድ ሻለቃ ዋና አዛዥ ኮሎኔል አሰፋ መኮንን በበኩላቸው የቀጠናውን የሰላምና የፀጥታ ሁኔታ ለማጠናከር አልሸባብን በመዋጋት እንዲሁም የኬላ ፍተሻዎችን በማጠናከር የህብረተሰቡን ሰላምና ደህንነት ማረጋገጥ እንደሚገባ ጠቁመዋል፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤ ተንቀሳ የፋና ድረ ቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!