Fana: At a Speed of Life!

አቶ እርስቱ ይርዳው በጌዴኦ ዞን የይርጋ ጨፌ የገጠር የለውጥ ማዕከል የግንባታ ሂደትን ጎበኙ

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 27 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)በደቡብ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ እርስቱ ይርዳው የተመራ ልዑክ በጌዴኦ ዞን የይርጋ ጨፌ የገጠር የለውጥ ማዕከል የግንባታ ሂደትን ጎበኙ።
የደቡብ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ እርስቱ ይርዳ በዲላ ከተማ ከ200 ሚሊየን በላይ ብር ለሚገነባው የንጹህ መጠጥ ውሀ ፕሮጀክት የመሰረት ድንጋይ አኑረዋል፡፡
ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ አቶ በወቅቱም ከዲላ ከተማ ነዋሪዎች እና አመራሮች ጋር በነበራቸው የውይይት መድረክ ላይ÷የበርካታ ዜጎችን የንጹህ መጠጥ ውሀ ችግር ይፈታል ተብሎ የሚጠበቀው ፕሮጀክት ስኬታማ እንዲሆን የክልሉ መንግሥት አስፈላጊውን ድጋፀፍ ያደርጋል ብለዋል፡፡
አብዛኛው ፕሮጀክቶች ከወሰን ማስከበር ጋር ተያይዞ የመዘግየት ሁኔታ ይስተዋላል ያሉት ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ ÷የመጠጥ ውሀ የመስመር ዝርጋታ በሚያልፍባቸው አካባቢዎች ህብረተሰቡ ምቹ ሁኔታ በመፍጠር አስፈላጊውን ትብብር ማድረግ እንዲችል ጥሪ አቅርበዋል፡፡
የከተማ ነዋሪዎችም መንግሥት ለበርካታ አመታት የንጹህ መጠጥ ውሃ ጥያቄያችን በሰጠው ምላሽ ተደስተናል ብለዋል፡፡
ፕሮጀክቱ ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ የበኩላቸውን ድጋፍ እንደሚያደርጉም የተናገሩት ነዋሪዎቹ ከዚህ ቀደምም ለከተማው የእሳት አደጋ መከላከያ ተሽከርካሪ በመግዛት ለመንግስት ያለንን አጋርነት ማሳየት ችለናልም ነው ያሉት።
የደቡብ ክልል ውሀ ማዕድን እና ኢነርጂ ቢሮ ሀላፊ ኢንጂነር አክሊሉ አዳኝ በበኩላቸው÷በክልሉ በአዝጋሚ ጉዞ ላይ የሚገኘውን የንጹህ መጠጥ ውሀ ተጠቃሚነት ለማሳደግ እየተሰራ ነው ብለዋል ፡፡
ይህ የሚገነባው የዲላ መጠጥ ውሀ ሳኒቴሽን እና ሀይጂን ፕሮጀክት 80 በመቶ ከአለም ባንክ በተገኘ ብድር እንዲሁም 20 በመቶ በክልል መንግስት የበጀት ምንጭ የሚገነባ ይሆናል ማለታቸውን ከደቡብ ክልል ኮሙዩኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳ
የፋና ድረ ቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለ
34,209
People Reached
661
Engagements
Boost Post
323
3 Comments
18 Shares
Like

Comment
Share
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.