Fana: At a Speed of Life!

መገናኛ ብዙኀን የተሳሳተ መረጃ ሊያስከትል የሚችለውን ሀገራዊ ቀውስ አስቀድሞ በመረዳት በየጊዜው የተጣለባቸውን ኃላፊነት እንዲወጡ ተጠየቀ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 27፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) መገናኛ ብዙኃን የተሳሳተና የተጋነነ መረጃ ሊያስከትል የሚችለውን ሀገራዊ ቀውስ አስቀድሞ በመረዳት በየጊዜው የተጣለባቸውን ኃላፊነት እንዲወጡ ተጠየቁ፡፡

ከኢትዮጵያ ሀይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጋር መገናኛ ብዙኀን በሃገራዊ ሳላምና በህዝባዊ አብሮነት ላይ ያተኮረ የውይይት መድረክ እየተካሄደ ነው።

በመድረኩ የሀይማኖት አባቶች፣ ከተለያዩ መገናኛ ብንዙኀን የስራ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች ታድመዋል።

በዚህ ወቅት መገናኛ ብዙኃን የሰዎችን ክብርና ሁለንተናዊ ደህንነት አደጋ ውስጥ የሚጥሉ መረጃዎችን ከማሰራጨት እንዲቆጠቡ መጠየቁን ኢዜአ ዘግቧል።

በዚህ ረገድ መገናኛ ብዙኀኑ ገለልተኛ ሆነው ሀገራዊ ሰላምና የህዝቦችን አብሮነት፤ አንድነት የሚያጠናክሩ ስራዎች ሊሰሩ ይገባል ተብሏል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.