የሀላባ ብሔረሰብ የዘመን መለወጫ የሴራ በዓል በአዲስ አበባ ተከበረ
አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 26፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ)የሀላባ ብሔረሰብ የዘመን መለወጫ የሴራ በዓል በአዲስ አበባ ተከበረ፡፡
በዚህ በዓል ላይ የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር ዶክተር ሂሩት ካሳው ፣ የሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ኤርጎጌ ተስፋዬ እና የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ኢንጅነር ታከለ ኡማ ተገኝተዋል፡፡
ኢንጅነር ታከለ ኡማ በበዓሉ ላይ ለታደሙ የሃላባ ብሔረሰብ ተወላጆች የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
በአዲስ አበባ የሚኖሩ የሃላባ ብሔረሰብ ተወላጆች የከተማ አስተዳደሩ የሚሰራቸውን ስራዎች በቀጣይነት እንደሚደግፉ ተናግረዋል፡፡
በበዓሉ ላይ የመንግስት ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ፣የብሔረሰቡ ተወላጆች እንዲሁም ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ታዳሚ ሆነዋል፡፡
የሴራ በዓል በየዓመቱ በታህሳስ ወር ወይም በብሄረሰቡ አጠራር መንገሳ በሚባለው ወር የሚከበር በዓል መሆኑን ከከንቲባ ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡