Fana: At a Speed of Life!

የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አገኘሁ ተሻገር በደቡብ ጎንደር ዞን የተፈጥሮ ሀብት ልማት ንቅናቄ አስጀመሩ

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 27 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ ጎንደር ዞን የዘንድሮ የተፈጥሮ ሀብት ልማት ንቅናቄ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አገኘሁ ተሻገርና ሌሎች ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች በተገኙበት በታች ጋይንት ወረዳ ተጀምሯል።

ለ20 ቀናት በሚከናወነው የተፈጥሮ ሀብት ልማት ስራ በታች ጋይንት ወረዳ ከሚገኙ 97 ተፋሰሶች በዚህ አመት 44 የሚሆኑት በተለያዩ የአፈርና ውሀ እቀባ ስራዎች ይሸፈናሉ ተብሏል።

ርዕሰ መስተዳድሩ የዚህ አመት የተፈጥሮ ሀብት ልማት ስራ ህብረተሰቡ በተፈጥሮ ሀብት ልማት ስራ ላይ በትጋት በመረባረብ የተመዘገበውን ድል በልማቱም ሊደግመው እንደሚገባም ገልፀዋል።

የተፋሰስ ልማት ስራዎችን በዘላቂነት ከመንከባከብ አኳያ የሚታዩ ችግሮችን በመቅረፍ የአርሶ አደሩን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በትኩረት ሊሰራ እንደሚገባም ርዕሰ መስተዳድሩ መናገራቸውን ኢብኮ ዘግቧል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳ
የፋና ድረ ቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.