Fana: At a Speed of Life!

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በየካ ክፍለ ከተማ አነስተኛ ገቢ ላላቸው ነዋሪዎች የበዓል ስጦታ አበረከተ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 27፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በየካ ክፍለ ከተማ ለ4 ሺህ 520 አነስተኛ ገቢ ላላቸው ነዋሪዎች ከ8 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት የበዓል ስጦታ አበረከተ፡፡

በስጦታ መርሐ ግብሩ ላይ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአገልግሎት ሰጪ ተቋማት አስተባባሪ አቶ ጃንጥራር አባይን ጨምሮ ሌሎች ኃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡

የክፍለ ከተማው ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አስፋው ተክሌ አነስተኛ ገቢ ካላቸው ነዋሪዎች ጋር በዓሉን ለማክበር ታቅዶ በጎ ፈቃደኞችን በማስተባበር የተሰራ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡

በዓሉን አስመልክቶም በዕለቱ ለ149 አነስተኛ ደመዎዝ ተከፋይ የመንግስት ሰራተኞች የገንዘብና የበዓል መዋያ ስጦታ እንደተበረከተላቸውም ተገልጿል፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.