Fana: At a Speed of Life!

የገና በዓል ሲከበር እሳትና ድንገተኛ አደጋዎች እንዳይከሰቱ ጥንቃቄ ማድረግ ያስፈልጋል– ኮሚሽኑ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 27፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ህብረተሰቡ የገና በዓልን ሲያከብር እሳትና ድንገተኛ አደጋዎች እንዳይከሰቱ ጥንቃቄ ማድረግ እንዳለበት የአዲስ አበባ የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አሳሰበ።
የአዲስ አበባ የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነት ቡድን መሪ አቶ ጉልላት ጌታነህ÷ ያለ ባለሙያ በቤት ውስጥ በተለይ ተጠጋግተው የተሰሩ ቤቶች ባሉባቸው መንደሮች ውስጥ ጥንቃቄ በጎደለው መልኩ የሚከናወኑ የኤሌክትሪክ ገመድ ዝርጋታዎች ለድንገተኛ የእሳት አደጋ ምክንያት ሊሆኑ እንደሚችሉ ተናግረዋል።
በተጨማሪም የማብሰያ ሲሊንደሮችን በጥንቃቄ አለመጠቀም እና እሳት ባለበት አካባቢ የቤት ውስጥ ቆሻሻ ማከማቸት ለድንገተኛ እሳት አደጋ እንደሚያጋልጥ አብራርተዋል።
በመሆኑም ህብረተሰቡ በዓሉን ሲያከብር አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንዲያደርግ ያሳሰቡት አቶ ጉልላት የምግብ ማብሰያዎችን ከተጠቀመን በኋላ በትክክል ማጥፋታችንን ማረጋጋጥ አለብን ብለዋል።
የእሳት አደጋ በሚከሰትበት ወቅትም በኮሚሽኑ የቀጥታ የስልክ መስመሮች 011 155 53 00 ወይም 011 156 86 01 እንዲሁም በነጻ የስልክ መስመር 939 በመደወል ማሳወቅ እንደሚገባ መናገራቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.