ዓለምአቀፋዊ ዜና

የኮሮና ቫይረስን መነሻ ለማጥናት ወደ ውሃን ያቀናው የዓለም ጤና ድርጅት ቡድን ወደ ከተማዋ መግቢያ ተከለከለ

By Meseret Awoke

January 06, 2021

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 28፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኮሮና ቫይረስን መነሻ ለማጥና ወደ ውሃን ከተማ ያቀናው የዓለም ጤና ድርጅት መርማሪ ቡድን ወደ ከተማዋ መግቢያ መከልከሉ ተሰማ፡፡

የዓለም ጤና ድርጅት እና ቻይና በውሃን ከተማ አጠቃላይ የቫይረሱ ስርጭትና ሁኔታ ላይ ጥናት የሚያካሂድ ቡድን ወደ ከተማ እንዲገባ መስማማታቸው ይታወሳል፡፡

ከልዑካን ቡድኑ መካከል አንደኛው የተመለሰ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ በሶስተኛ ሃገር አድርጎ ወደ ቻይና ለመግባት እየሞከረ መሆኑንም መረጃዎች ያመላክታል፡፡

የዓለም ጤና ድርጅት ችግሩ ከቪዛ ጋር ያሉ ጉዳዮች ባለመጠናቀቃቸው ሳቢያ የተፈጠረ መሆኑን ይገልጻል፡፡

የዓለም የጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም በበኩላቸው ቻይና ቡድኑ ወደ ከተማ ይገባ ዘንድ የሚያስችሉ ሂደቶችን በጊዜ ባለማጠናቀቋ ማዘናቸውን ገልጸዋል፡፡

ድርጅቱ 10 የዓለም አቀፍ ባለሙያዎችን ቡድን የቫይረሱን አመጣጥና አጠቃላይ ሁኔታ ለማጥናት በማለም ወደ ቻይና ለመላክ ለወራት ያህል ሲሰራ መቆየቱ የሚታወስ ነው፡፡

ምንጭ፡- ቢቢሲ

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤ ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!