የሀገር ውስጥ ዜና

የአማራ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር አገኘሁ ተሻገር ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ

By Tibebu Kebede

January 06, 2021

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 28 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የአማራ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር አገኘሁ ተሻገር ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።

የልደት በዓልን አንድነትን የሚሸረሽሩ ኃይሎችን በመታገል፣ የተፈናቀሉ ወገኖችን በመጠየቅና በመደገፍ ሊሆን እንደሚገባም ጥሪ አቅርበዋል።

የክልሉ መንግሥት የአማራ ሕዝብን ጥቅምና ክብር ለማስጠበቅ ከምንጊዜውም በበለጠ በቁርጠኝነት እየሠራ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡

ሕዝቡም ለዚህ ተባባሪ መሆን ይገባዋል ማለታቸውን አብመድ ዘግቧል፡፡

የኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል የሰላምና የደስታ እንዲሆንም መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤ ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!