Fana: At a Speed of Life!

ህብረተሰቡ በየአካባቢው በተዋቀረው አደረጃጀት በመጠቀም በልማቱ ተሳታፊና ተጠቃሚ እንዲሆን ጥሪ ቀረበ

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 28 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ በህብረተሰብ ተሳታፊነትና ተጠቃሚነት ዙሪያ ከሁሉም ክፍለ ከተሞች ከተውጣጡ የብሎክ አደረጃጀት ተወካዮች ጋር ተወያይተዋል።

ምክትል ከንቲባዋ በዚህ ወቅትለፅንፈኝነት የተመቸ ሃገር አለ ባይባልም በኢትዮጵያ ነባራዊ ሁኔታም ፅንፈኝነት ሃገር ያፈርስ እንደሆነ እንጅ አይገነባም ብለዋል፡፡

ለውጡ ብዙ ዋጋ ቢያስከፍልም በቁርጠኝነት የተያዘውና የመሀሉን መንገድ የሚከተለው ሃገራዊ ለውጥ በአቢዮት ሊፈጠር የሚችለውን ሃገራዊ ውድመት ማስቀረቱን ምክትል ከንቲባዋ አስታውቀዋል፡፡

የታችኛው የብሎክ አደረጃጀት ሰላምንና ፀጥታን በማረጋገጥ እንዲሁም ህገወጥነትን በመድፈቅ በኩል ያሳየው ለውጥ አበረታች መሆኑን የጠቆሙት ወይዘሮ አዳነች አደረጃጀቱ በአካባቢ ልማት ህብረተሰቡን ተሳታፊና ተጠቃሚ እንዲሆን የተጀመረው ጥረት ተጠናክሮ እንዲቀጥል አሳስበዋል፡፡

የአዲስ አበባ ብልፅግና ፓርቲ ፅህፈት ቤት ሀላፊ አቶ መለሰ አለሙ በበኩላቸው ብዝሃ ሆና የተፈጠረችዋን ኢትዮጵያን ለመገንባት የሁሉም ርብርብ ወሳኝ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

ዋና ዋና የህዝብ ጥያቄዎች ሲቀረፉ በግለሰብ ደረጃ ያሉ ፍላጎቶችም ስለሚሟሉ ለህዝብ ጥቅም ትኩረት መስጠት እንደሚገባም አስረድተዋል፡፡

በተበተነ አቅም የተደመረ ውጤት ማስመዝገብ እንደማይቻል መገንዘብ እንደሚገባም መናገራቸውን ከከተማዋ ፕሬስ ሴክሬታሪያት ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

የብሎክ አደረጃጀት ለከተማዋ ጥፋት ደግሰው የነበሩ እኩዮችን ዓላማ በንቃት በመከታተል ማክሸፉን የገለፁት አቶ መለሰ ለህዝቡ የበለጠ የቀረበ አደረጃጀት እንደመሆኑ በቀጣይም ብዙ መስራት እንደሚጠበቅበት መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.