Fana: At a Speed of Life!

የተፃፈበትን የብር ኖት አትቀበሉ በሚል እየተሰረጨ ያለው መረጃ ሀሰት ነው- ብሄራዊ ባንክ

አዲስ አበባ ፣ታህሳስ 28 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ “የተፃፈበትን የብር ኖት አትቀበሉ” በሚል እየተሰረጨ ያለው መረጃ ሀሰት መሆኑን የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ ገለጸ።
ብሄራዊ ይህኑ እየተሰራጨ ያለ መረጃ በተመለከተ ዛሬ የፕሬስ መግለጫ አውጥቷል።
በመግለጫው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ አዲስ የብር ኖት አሳትሞ ሥራ ላይ ማዋሉን አስታውሷል።
ከመስከረም 6 ቀን 2013 ዓ.ም እስከ ታህሳስ 6 ቀን 2013 ዓ.ም በመላ ሀገሪቱ የብር ኖት ቅያሪ ሲያካሂድ መቆየቱንም ነው የገለፀው፡፡
የብር ኖት በከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ የሚታተም የሕዝብ ሀብት ነው።
በመሆኑም በጥንቃቄ ተይዞ ሕብረተሰቡ ለረጅም ጊዜ ሊገለገልበት ይገባል።
ከዚህ አንፃር ሆን ተብሎ ወይም በቸልተኝነት በብር ኖት ላይ ጉዳት እንዳይደርስበት እንዲሁም ብዛት ያለው ገንዘብ ሕግን ባልተከተለ መልኩ ያለአግባብ እንዳይከማች ለማድረግ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ መመሪያ ቁጥር CMD/01/2020 ማውጣቱንም ገልጿል፡፡
በመሆኑም፣ የብር ኖቱ ረጅም ጊዜ እንዲያገለግል በማስብ፡
1.በብር ኖቱ ላይ መፃፍ፣ መቅደድና በቀለም ማበላሸት፣ የትኛውንም ዓይነት ጉዳት ማድረስና ምልክቶቹን ያለፈቃድ ማባዛት የተከለከለና በሕግ የሚያስጠይቅ መሆኑን፣
2. ለማስታወቂያ ሥራ ከተፈለገ ግን ለማባዛት የባንኩን ፈቃድ ማግኘት አስፈላጊ መሆኑን፣
3. በጣም የተጎዱ የብር ኖቶች ሲያጋጥሙ ከዝውውር ስለሚወጡበት ሁኔታ ዝርዝር መመሪያ እየተዘጋጀ መሆኑን፣እና
4. ባንኩ መመሪያውን ወደ አማርኛ በማስተርጎምና በማብራራት ስለብር ኖት አጠቃቀም በየጊዜው ለህብረተሰቡ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራ የሚሠራ መሆኑን፣ እየገለፅን “የተፃፈበትን የብር ኖት አትቀበሉ” እየተባለ የሚናፈሰው ወሬ መሠረተ ቢስ መሆኑን ለመግለፅ ሲል ለኢዜአ በላከው መግለጫ ላይ አስታውቋል።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.