Fana: At a Speed of Life!

ህወሃት ከብልጽግና ፓርቲ ጋር እንደማይዋሃድ አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 26፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ለሁለት ቀናት ያካሄደውን አስቸኳይ ድርጅታዊ ጉባኤ አጠናቋል፡፡

በማጠቃለያው ባወጣው መግለጫም ከብልጽግና ፓርቲ ጋር የዓላማና የመስመር ልዩነት ስላለው እንደማይዋሃድ አስታውቋል።

ከፌዴራል መንግስት ጋር የሚኖረው ግንኙነትም ህግና ህገ-መንግስትን መሰረት ያደረገ እንደሚሆን ያመለከተው መግለጫው ከዚህ ውጭ የሚኖር እንቅስቃሴ ተቀባይነት እንደማይኖረው አመልክቷል።

ኢህአደግን የመሰረቱ የአራቱ ድርጅቶችን የጋራ ሀብት ህግና ስርአት በተከተለ መንገድ ድርሻውን እንደሚያስመልስም በአቋም መግለጫው አስታውቋል።

የኢህአዴግን መፍረስ ተከትሎ ህወሓት ከሌሎች ፈዴራላዊ ሀይሎች ጋር በፎረም፣በጥምረትና በግንባር ደረጃ ስትራተጂካዊ ግንኙነት ለመመስረት መወሰኑንም ገልጿል።

ምንጭ፡- ኢዜአ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.