Fana: At a Speed of Life!

የገና በዓል ከጦር ጉዳተኞች ጋር ተከበረ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 29፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርና የሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የገናን በዓልን ከጦር ጉዳተኞች ጋር አከበሩ።
የአዲስ አበባ ከተማ መስተዳድር የአካል ጉዳተኞችን ፍትሃዊ ተጠቃሚነት እና ተሳታፊነትን ማረጋገጥ ኃላፊነቱ መሆኑንና ለዚህም ትኩረት ሰጥቶ የሚሰራ መሆኑን ገልጿል።
በመሆኑም ይህንን ዓላማ ተግባራዊ ያደረገ የበዓል ፕሮግራም ከጦር ጉዳተኞች ጋር አክብሯል።
በክብረ በዓሉ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ፣ የሰራተኛ እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ኤርጎጌ ተስፋዬ፣ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ዶክተር ሳሙኤል ኡርቃ ፣ የቀደሞ እና የአሁን የጦር ጄኔራሎች እና ከ141 በላይ የጦር ጉዳተኞች ተገኝተዋል።
በወቅቱም ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ ÷ ጀግንነት የትውልድ ቅብብሎሽ ሲሉ ገልጸዋል።
ይህ የትውልድ የጀግንነትና የመስዋዕትነት ቅብብሎሽ ኢትዮጵያና ህዝቦቿ በዓለም ታፍረን እና ተከብረን እንድንኖር አድርጎናል ብለዋል።
የጦር ጉዳተኞቹ ታላላቅ ጀብድ የሰሩና ለአገር እና ለህዝብ ህይወታቸውን እና አካላቸውን መስዋዕት ያደረጉ ጀግኖች የአገር ኩራት እንደሆኑም አመልክተዋል።
ጀግንነት የትውልድ ቅብብሎሽ በመሆኑ በዚሁ ሂደት ኢትዮጵያና ህዝቦቿ ተከብረው ዘልቀዋል ብለዋል።
ለዚህ ክብር የጦር ጉዳተኞቹ ታላላቅ ጀብድ የሰሩና ለአገርና ለህዝብ ህይወታቸውንና አካላቸውን መስዋዕት ያደረጉ መሆናቸውንም ጠቅሰዋል።
በመሆኑም ከጦር ጉዳተኞች ጋር በዓል ማክበር ብቻ ሳይሆን ማዕከሉ ለትውልድ እንዲያገለግል ብዙዎች የሚማሩበትና የዜጎች ኩራት ሆኖ እንዲቀጥል ይደረጋልም ነው ያሉት።
በበአል ፕሮግራሙ ላይ ቀደም ሲል የነበሩትና ፈርሰው የነበሩ የብሄራዊ ጀግኖች አምባ እና የህጻናት አምባ ማህበራት መልሶ መቋቋሙም ተነግሯል፡፡
ከዚያም ባለፈ የቀደሙት እና አሁን ያሉት የጦር ጉዳተኞች ተጠቃሚ የሚያደርጉ እቅዶችም ተነድፈዋል፡፡
በዚህም የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርና የፌዴራል ፖሊስ ከሰራተኛ እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ጋር በመሆን ለተግባራዊነቱ እንደሚሰራ ተገልጿል፡፡
በፈቲያ አብደላ አና ፍሬህይወት ሰፊው
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.