Fana: At a Speed of Life!

ከተማ አስተዳደሩ ከ8 ሺህ በላይ ወጣቶችን ከጎዳና አንስቶ እያሰለጠነ ነው-ወ/ሮ አዳነች አቤቤ

አዲስ አበባ ፣ታህሳስ 29 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በ2013 በጀት ዓመት 8 ሺህ 286 ወጣቶችን ከጎዳና አንስቶ እያሰለጠነ እንደሚገኝ ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነችአቤቤ ገለጹ።
የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አበቤ ይህንን የገለጹት በቃሊቲ ጊዜያዊ ማቆያ ከሚገኙ ከጎዳና ከተነሱ ዜጎች ጋር የገና በዓልን በአከበሩበት ወቅት ነው ።
ከምክትል ከንቲባዋ በተጨማሪ ሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትሯ ዶክተር ኤርጎጌ ተስፋዬ ከጎዳና ከተነሱ ዜጎች ጋር ማዕድ በማጋራት በተከበረው የገና በዓል ላይ ተገኝተዋል።
የበዓል ፕሮግራም የተከናወነው የገና በዓልን ምክንያት በማድረግ የጎዳና ተዳዳሪዎችን በማብቃት እና በማሸጋገር ፍትሃዊ የሃብት ክፍፍልን እናረጋግጥ በሚል መሪ ሃሳብ መሆኑ ተመላክቷል።
በመርሐግብሩ ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ÷ በተያዘዉ በጀት ዓመት 8 ሺህ 286 በጎዳና ይኖሩ የነበሩ ዜጎችን በማንሳት የሙያ ክህሎት እና የስነ-ልቦና ስልጠናዎች መሰጠቱን ገልጸዋል ።
የሙያ ስልጠናዎቹ በደረቅ ቆሻሻ፣ አረንጓዴ ልማት፣ጋርመንት ፣ የሌዘር ስራዎች እና መንገድ ጥርጊያ ላይ ያተኮሩ መሆናቸውንም አመላክተዋል።
በዚህም እስካሁን በሰባት ክፍለ ከተሞች እና በአቃቂ ጊዜያዊ ማዕከል 3 ሺህ 966 የሚሆኑት ወጣቶች ተገቢዉን የሙያ እና የስነ-ልቦና ስልጠናቸዉን አጠናቀዉ ለስሯ ዝግጁ መደረጋቸዉ ተገልጿል።
ቀሪዎቹም በተለያዩ ዙሮች ተመሳሳይ ስልጠና እና ክህሎት እየተሰጣቸዉ እንደሚገኝ ም ነው ከንቲባዋ የገለጹት።
ጎዳና ጊዜያዊ የህይወት መምሪያችሁ ሆኖ ቆይቷል ያሉት ምክትል ከንቲባዋ አሁን ያ ጊዜ አልፎ በሌላ የህይወት ምዕርፍ ላይ ተገኝታችኋል ብለዋል።
ወይዘሮ አዳነች አያይዘውም ፈተና ለእናንተ አዲስ አይደለም በጎዳናም ብዙ ፈተና አልፋችሁ መጥታችኋል ስለሆነም የወሰዳችሁትን ስልጠና ወደ ተግባር ቀይራችሁ ወደ ስራ አለም ስትገቡ ለሚገጥማቸዉ ፈተና እጅ ሳትሰጡ እራሳችሁንና ሀገራችሁን እንድትጠቅሙ ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል።
ለዚህም ከተማ አስተዳደሩም ከጎናችሁ ነው ሲሉ ገልጸዋል።
ወጣቶቹም በበኩላቸው ወደ ስራ አለም ለመቀላቀል በቂ ክህሎት መያዛቸዉን ጠቅሰዉ የስራ እድል እንዲመቻችላቸዉ እና ትኩረት እዲሰጠዉ ጠይቀዋል።
በፍሬህይወት ሰፊዉ
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.