Fana: At a Speed of Life!

ወጣቱ ትውልድ፣ ታሪኩን፣ ባህሉንና እሴቱን በመጠበቅና በማስጠበቅ ለቀጣዩ ትውልድ ሊያስተላልፍ ይገባል

አዲስ አበባ ፣ታህሳስ 29 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ወጣቱ ትውልድ፣ ታሪኩን፣ ባህሉንና እሴቱን በመጠበቅና በማስጠበቅ ለቀጣዩ ትውልድ ሊያስተላልፍ እንደሚገባ የሀረሪ ክልል ባህል ቅርስና ቱሪዝም ቢሮ ገለፀ።
134ኛው የጨለንቆ ሰማዕታት ቀን በልዩ ልዩ ዝግጅቶች በደማቅ ሁኔታ በክልሉ ተከብሮ ውሏል።
የክልሉ ባህል ቅርስና ቱሪዝም ቢሮ ሃላፊ አቶ ዲኒ ረመዳን ÷ የሀረሪ ህዝብ የራሱ የማንነት መገለጫ አኩሪ ብሄረሰባዊ እሴቶች ያሉት ነባርና ቀደምት ህዝቦች ውስጥ አንዱ ነው ብለዋል።
ህዝቡም ከኦሮሞ፣ ከሶማሌ፣ ከአፋርና፣ ከአርጎባ ህዝቦች ጋር ረዥም ዘመናትን ያስቆጠረና እጅግ የጠበቀ ታሪካዊ፣ ባህላዊ፣ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ መስተጋብሮች እንዳሉትም ገልጸዋል።
ታሪክ ያለፈውንና የአሁኑን ትውልድ የሚያገናኝ ድልድይ በመሆኑ የምንኮራባቸው እሴቶቻችንንና ባህሎቻችን በአለም አቀፍ ደረጃ አውቅና ያገኘንበት በመሆኑና የአሁኗ ኢትዮጵያ ያለፈ ታሪካችንን ማሳያ እንጂ የአንድ ጀንበር ውጤት አለመሆኑን መገንዘብ ያስፈልጋልም ነው ያሉት።
በመሆኑም ካለፉት ስህተቶች በመማር ለመጪው ትውልድ የምትመች ሐገርን መፍጠር ያስፈልጋል ሲሉም የቢሮ ሃላፊው ገልፀዋል።
የጨለንቆ ሰማእታት ቀን ሲዘከር ኢትዮጵያ ባለፉት አመታት ያስመዘገበቻቸውን የማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖሊቲካዊ ለውጦችን አስጠብቆ ለማወቆየትና ባለፉት አመታት የታዩ ስህተቶችን በማረምና የመጪውን ትውልድ ጥቅምና ፍላጎት በዘላቂነት የሚያስከብር አስተማማኝ መሰረት በመገንባት መሆን አለበትም ነው ያሉት።
በዚህም ሰላም፣ ዲሞክራሲ፣ ህብረ ሃገራዊ አንድነት፤ የዜጎች ክብር ፍትህና የጋራ ብልጽግና የተረጋገጠባት ሐገር እውን በማድረግ ነው ሲሉ ገልጸዋል።
የክልሉ ባህል ቅርስና ቱሪዝም ቢሮ ምክትል ቢሮ ሃላፊ አቶ አዩብ አብዱላሂ በበኩላቸው÷የጨለንቆ ሰማእታትን ቀን ስናከብር የመልከአ -ምድር አቀማመጥ ሳይበግራቸው፣ የብሄርና የቋንቋ ልዩነቶች ሳይከፋፍላቸው ለጋራ አላማ የተዋደቁ የምስራቅ ኢትዮጰያ ህዝቦች ወንድማማችነትና አንድነት እንዲሁም የባህል ቁርኝትን ለማደስም ጭምር ነው ማለታቸውን ከሀረሪ ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤትያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.