የሀገር ውስጥ ዜና

ሰባት የውጭ ሀገር ዜግነት ያላቸው ግለሰቦች በባዛሮች ጥራታቸውና ፈዋሽነታቸው ያልተረጋገጡ ምርቶችን ሲሸጡ በቁጥጥር ስር ዋሉ

By Tibebu Kebede

January 05, 2020

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 26፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ)ሰባት የውጭ ሀገር ዜግነት ያላቸው ግለሰቦች በባዛሮች ጥራታቸውና ፈዋሽነታቸው ያልተረጋገጡ ምርቶችን ሲሸጡ በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡

የኢትዮጵያ የምግብና መድኃኒት ባለስልጣን ከፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ጋር በመተባበር ስምንት ዓይነት ያህል የባህላዊ መድኃኒቶች ጸጉርን ለማከምና ለማሳጅ ይረዳል በሚል ሲሸጡ በመገኘታቸው በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተጠቁሟል፡፡