Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያን ጨምሮ በተለያዩ ቦታዎች ከተከሰከሱ አውሮፕላኖች ጋር በተያያዘ ቦይንግ 2 ነጥብ 5 ቢሊየን ዶላር ሊከፍል ነው

አዲስ አበባ ፣ታህሳስ 30 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ቦይንግ ኩባንያ ኢትዮጵያን ጨምሮ በተለያዩ አካባቢዎች ከተከሰከሱት 737 ማክስ አውሮፕላኖች ጋር በተያያዘ የአውሮፕላኖችን የዲዛይን መረጃ በመደበቁ 2 ነጥብ 5 ቢሊየን ዶላር ካሳ ሊከፍል ነው።
ከግልፅነት ይልቅ ትርፍን አስበልጧል ሲል ቦይንግን የከሰሰው የአሜሪካ ፍትህ መስሪያ ቤት የበርካቶች ህይወት ያለፈባቸውን የአውሮፕላን አደጋዎች ያስከተሉ የ737 ማክስ አውሮፕላኖች ላይ ክትትልና ቁጥጥር እንዳይደረግ መከልከሉን ገልጿል።
ከ2 ነጥብ 5 ቢሊየን ዶላሩ መካከል 500 ሚሊየን ዶላሩ በ737 ማክስ አውሮፕላን አደጋዎች ህይወታቸውን ላጡ መንገደኛ ቤተሰቦች የሚከፈል ካሳ ነው ተብሏል።
1 ነጥብ 7 ቢሊየን ዶላሩ ደግሞ ለቦይንግ ኩባንያ አየር መንገዶች የሚከፈል መሆኑንም ቢቢሲ በዘገባው ላይ አስፍሯል።
እንዲሁም ቦይንግ ኩባንያ ለፈፀማቸው ጥፋቶች 243 ነጥብ 6 ሚሊየን ዶላር እንደሚቀጣ ነው የተነገረው።
የቦይንግ ኩባንያ ዋና ስራ አስፈፃሚ ዴቪድ ካልሆውን ወደዚህ ውሳኔ ሀሳብ መግባታችን ትክክል መሆኑ ጠንካራ እምነቴ ነው ያሉ ሲሆን እርምጃው ከእሴታችን እና ከሚጠበቅን ነገር አንፃር ለፈፀምነው ስህተት እውቅና የሚሰጥ ነው ብለዋል።

 

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.