ዓለምአቀፋዊ ዜና

ትራምፕ ስልጣናቸውን እንደሚለቁ ቃል ገቡ

By Meseret Awoke

January 08, 2021

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 30፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ሰላማዊ የስልጣን ሽግግር ለማድረግ ቃል ገብተዋል፡፡

ፕሬዚዳንቱ ደጋፊዎቻቸው በካፒቶል ሒል ከገቡ በኋላ በዓለም መንግስታት ውግዘት የደረሰባቸው ሲሆን፤ በደረሰው ጉዳትም አንድ የካፒቶል ሒል ፖሊስን ጨምሮ የአምስት ሰዎች ህይወት ማለፉም ተነግሯል፡፡

ትናንት ምሽትም ሁለት የፕሬዚዳንቱ የካቢኔ አባላቶች ሥልጣናቸውን በገዛ ፈቃዳቸው ለቀዋል፡፡

የአሜሪካ ኮንግረስ ጆ ባይደን እና ካማላ ሀሪስን ቀጣዮቹ የአሜሪካ ፕሬዚዳንት እና ምክትል ፕሬዚዳንትነት አጽድቋል፡፡

ፕሬዚዳንት ትራምፕም ከቀናት በኋላ ስልጣናቸውን ለቀጣዩ የአሜሪካ ፕሬዚዳንት እንደሚያስረክቡ ተናግረዋል፡፡

”በአሁኑ ወቅት ሰላማዊ፣ ሥርዓቱን የጠበቀ እና እንከን የለሽ የሥልጣን ሽግግርን ማረጋገጥ ነው” ብለዋል፡፡ ምንጭ፡- ቢቢሲ ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤ ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!