Fana: At a Speed of Life!

ሱዳን ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን የድንበር ጉዳይ በዲፕሎማሲና በውይይት እንድትፈታ ደቡብ ሱዳን አሳሰበች

አዲስ አበባ ፣ታህሳስ 30 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የደቡብ ሱዳን ፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪር ሱዳን ከድንበር ጋር ተይይዞ ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ጉዳይ በዲፕሎማሲና በውይይት እንድትፈታ አሳሰቡ።

ፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪር በሱዳን ሉዓላዊ ምክር ቤት አባል በሆኑት ሻምስ ል ዲን ካባሺ የተመራ ልዑክ በፅህፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል።

በዚህ ወቅትም በሁለትዮሽ እና ቀጠናዊ ጉዳዮች ዙሪያ ምክክር አድርገዋል።

ፕሬዚዳንቱ የሱዳን ሉዓላዊ ምክር ቤት ከኢትዮጵያ ጋር ያለውን የድንበር ጉዳይ በሰላማዊ መንገድ በዲፕሎማሲና በውይይት እንዲፈታ ነው ያሳሰቡት።

በቀጠናው ምንም አይነት ጦርነት አያስፈልግም ያሉት ፕሬዚዳንቱ ሀገራቱ የድንበር ጉዳዩን በሰላማዊ መንገድ መፍታት አለባቸው ብለዋል።

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.