Fana: At a Speed of Life!

ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ በግማሽ በጀት ዓመቱ ውስጥ በአዲስ አበባ ከተማ ብቻ ከ1ነጥብ3 ቢሊየን ብር በላይ ተሰበሰበ

አዲስ አበባ ፣ታህሳስ 30 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ በግማሽ በጀት ዓመቱ ውስጥ በአዲስ አበባ ከተማ ብቻ ከ1ነጥብ3 ቢሊየን ብር በላይ መሰብሰቡ ተገለፀ፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ህዝባዊ ተሳትፎ ማስተባበሪያ ፅህፈት ቤት እንደገለፀው÷ በስድስት ወራት በከተማው በቦንድ ግዢ ሽያጭ እና በስጦታ የተሰበሰበው ገንዘብ ባለፉት 8 ዓመታት በድምሩ ከተሰበሰበው የሚበልጥ ነው፡፡
ከ2003 ዓ.ም ዓምሌ ወር እስከ 2012 ዓ.ም ሃምሌ ወር ባሉ ዓመታት በከተማዋ የተሰበሰበው 1 ነጥብ 1ቢሊየን ብር እንደነበር ታውቋል፡፡
የህዝባዊ ተሳትፎ ማስተባበሪያ ፅህፈት ቤቱ ሓላፊ አቶ ምስክር ነጋሽ እንደተናገሩት÷ ለገቢው ማደግ ምክንያት መንግስት ፕሮጀክቱን በግልፅነት መምራት መሆኑን ተናግረዋል፡፡
ፕሮጀክቱ ላይ የነበሩ ችግሮች ይፋ ተደርገው የማስተካከያ እርምጃ በመውሰድ በህዝብ እና በመንግስት መካከል መተማመን እንዲፈጠር አድርጓል ብለዋል፡፡
የግድቡ የመጀመሪያ ዙር የውሃ ሙሌት በስኬት መከናወንም ማህበረሰቡ ከፍተኛ ድጋፍ እንዲያደርግ አስችሎታል ነው ያሉት፡፡
በዚህም በ2013 ዓ.ም በጀት ዓመት 789 ሚሊየን ብር እሰበስባለው ያለው ከተማ አስተዳደሩ በግማሽ ዓመት ውስጥ 1 ነጥብ 3 ቢሊየን ብር ለመሰብሰብ ችሏል፡፡
በአልዓዛር ታደለ
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.