የሀገር ውስጥ ዜና

ምክትል ጠ/ሚ ደመቀ መኮንን ከአውሮፓ ህብረት የውጭ ጉዳይ እና የፀጥታ ፖሊሲ ከፍተኛ ተወካይ ጋር ተወያዩ

By Tibebu Kebede

January 08, 2021

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 30 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ከአውሮፓ ህብረት የውጭ ጉዳይ እና የፀጥታ ፖሊሲ ከፍተኛ ተወካይ ጆሴፍ ቦረል ጋር በትግራይ ክልል ወቅታዊ ሁኔታ ላይ በስልክ ተወያዩ።

አቶ ደመቀ ክላስተርን መሠረት ባደረገ የማስተባበር ዘዴ እየተተገበረ ባለው የክልሉ የመልሶ ግንባታና መልሶ ማቋቋም ሥራዎች እንዲሁም በክልሉ የሰብአዊ ድጋፍ ለማድረስ እየተከናወኑ ባሉት ሥራዎች ዙሪያ ገለፃ አድርገዋል ፡፡

አያይዘውም በክልሉ ያሉ ሰብዓዊ ፍላጎቶችን ለማሟላት መንግስት እና ግብረ ሰናይ ድርጅቶች በቅንጅት እየሰሩ መሆኑንም አብራርተዋል።

በውይይቱ ወቅት በትግራይ ክልል የሰብዓዊ ዕርዳታ ማድረስ ላይ የተጀመሩ ጥረቶችን ለማጠናከር እና በቅርበት መስራታቸውን ለመቀጠል ተስማምተዋል።

በተጨማሪም በኢትዮጵያና በአውሮፓ ህብረት መካከል የጠበቀ ትብብርን ለማጠናከር መስማማታቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ፅህፈት ቤት መረጃ ያመላክታል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤ ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!