ዓለምአቀፋዊ ዜና

የእንግሊዙ ሚኒስትር ለኮቪድ 19 የተሰራው ክትባት እንደ አዲስ የተከሰተውን ቫይረስ ላይከላከል ይችላል ሲሉ ተናገሩ

By Tibebu Kebede

January 09, 2021

አዲስ አበባ ፣ ጥር 1 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ለኮቪድ 19 የተሰራው ክትባት እንደ አዲስ የተከሰተውን የኮሮና ቫይረስ ላይከላከል ይችላል የሚል ስጋት እንዳላቸው አንድ የእንግሊዝ ሚኒስትር ተናገሩ ።

ስማቸውን ያልተጠቀሱት ሚኒስትር እንዳሉት የተሰራው አዲሱ ክትባት በሚፈለገው ደረጃ ቫይረሱን ላይመክት ወይም በሚፈለገው መንገድ ምላሽ ላይሰጥ ይችላል የሚል ስጋት በባለሙያዎች ዘንድ ፈጥሯል።

ሬውተርስ እንደዘገበው ክትባቱን የሰሩት ባለሙያዎች አዲሱ ክትባት አዲስ ባህሪን ይዞ በመጣው እና ተላላፊነቱ እና አደገኝነቱ የከፋ በሆነው የኮሮና ቫይረስ ተጠቂዎች ላይ የሚያመጣውን ውጤት ለማየት እየሰሩ ነው።

አዲሱ የኮሮና ቫይረስ ዝርያ በደቡብ አፍሪካ እና በብሪታንያ የታየ ሲሆን በዓለም ላይ አዲስ ስጋትን ፈጥሯል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤ ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!