Fana: At a Speed of Life!

በአዲስ አበባ ለሀሠተኛ ሰነድ ማዘጋጃነት ሲውሉ የነበሩ ቲተሮችና ኮምፒውተሮች ከ5 ተጠርጣሪዎች ጋር ተያዙ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 1 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን በልደታ ክፍለ ከተማ በሀሠተኛ መንጃ ፈቃድ ሲያሽከርክር ከነበረ አሽከርካሪ በመነሳት በተሠራ ዘመቻ ለሀሠተኛ ሰነድ ማዘጋጃነት ሲውሉ የነበሩ የተለያዩ ቲተሮችና ኮምፒውተሮች ከአምስት ተጠርጣሪዎች ጋር መያዙን አስታወቀ።

በክፍለ ከተማው ወረዳ 10 ተግባር ዕድ አካባቢ በሀሠተኛ መንጃ ፈቃድ ሲያሽከረክር የነበረ ተጠርጣሪ በትራፊክ ፖሊስ አባላት በቁጥጥር ስር ይውላል፡፡

ፖሊስም ይህን ተጠርጣሪ መነሻ በማድረግ ባደረገው የምርመራ ማስፋት ተግባር በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 4 ጎላጎል ህንፃ አካባቢ ከሚገኝ አንድ የንግድ ቤት የፍርድ ቤት መበርበሪያ ትዕዛዝ በመያዝ ባደረገው ፍተሻ ሀሠተኛ ሰነዶችን ለማዘጋጀት ጥቅም ላይ ሲውሉ የነበሩ ኮምፒዩተሮች፣ እስካነርና ፕሪንተር ማግኘቱን አስታውቋል፡፡

ተጠርጣሪዎቹ ለወንጀል ተግባር ሊውሉ የነበሩ የተለያዩ ተቋማት ቲተሮች ያዘጋጁ ሲሆን ከእነዚህም ውስጥ በአዲስ አበባ አስተዳደር የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 11 አስተዳደር ጽ/ቤት፣ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲ የፌደራል ከፍተኛ መጀመሪያ ፍርድ ቤት የሚሉ፣ መልካሙ በቃና አጋ የሚል የጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 11 ዋና ስራ አስፈጻሚ እና ሄራን ህትመትና ማስታወቂያ ስራ የሚሉ የተለያዩ ቲተሮች እና ሌሎች ሀሠተኛ ሰነዶችን ከአራት ተጠርጣሪዎች ጋር በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ እያደረገ እንደሚገኝ የልደታ ክፍል ከተማ ፖሊስ መምሪያ የልዩ ልዩ ወንጀሎች ምርመራ ቲም ኃላፊ ኢንስፔክተር ታምራት ቻለው ተናግረዋል።

ሀሠተኛ ሰነድ ማዘጋጀትም ሆነ በሀሠተኛ ሰነድ መገልገል ወንጀል መሆኑን በመገንዘብ ህብረተሰቡ ሀሠተኛ ሰነድ እያዘጋጁ ሰዎችን የሚያታልሉ ግለሰቦችን ለፖሊስ ጥቆማ በመስጠት በህግ እንዲጠየቁ እንዱያደርግም ጠይቀዋል፡፡

ለመንገድ ላይ ትራፊክ አደጋ መከሰት አንዱ ምክንያት በሀሠተኛ መንጃ ፈቃድ ማሽከርከር በመሆኑ በትኩረት ሊሰራበት ይገባል ማለታቸውን ከኮሚሽኑ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.