Fana: At a Speed of Life!

አቶ ደመቀ መኮንን ከፐብሊክ ዲፕሎማሲ ክላስተር አስተባባሪዎች ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ጥር 1፣ 2013 (ኤፍቢሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ከፐብሊክ ዲፕሎማሲ ቡድን የክላስተር አስተባባሪዎች ጋር ተገናኝተው ተወያዩ።

አቶ ደመቀ በውይይታቸው በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ለተሰብሳቢዎቹ ዝርዝር ገለፃ አድርገዋል።

የውይይቱ ዋና ዓላማ የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም ለማስከበር የፐብሊክ ዲፕሎማሲ ቡድን ሊያበረክት በሚችላቸው አጃንዳዎች ላይ ያተኮረ ነው።

በውይይቱ የየክላስተር አስተባባሪዎች ከፐብሊክ ዲፕሎማሲ ቡድን ከሚጠበቀው አስተዋጽኦ አንጻር ያዘጋጁትንና ትኩረት ተሰጥቶ የሚከናወኑ የሥራ ዕቅዶቻቸውን በዝርዝር ያቀረቡ ሲሆን፤  የታቀዱት ሥራዎች እንዲፈፀሙ  በሚገባው ቅንጅት  ላይም  ምክክር ተደርጓል።

አቶ ደመቀ የክላስተር አስተባባሪዎቹ ላቀረቧቸው የሥራ ዕቅዶች አመስግነው በቀጣይ  የፐብሊክ ዲፕሎማሲ ቡድኑ የሚያደርገውን የሥራ እንቅስቃሴ ይበልጥ ማጠናከር የሚያስችሉ ሁኔታች እንዲመቻቹ ሚኒስቴር መሥሪቤታቸው አስፈላጊውን ሁሉ እንደሚያደርግ ቃል መግባታቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

የኢትዮጵያ የፐብሊክ ዲፕሎማሲ ቡድን ከተመሰረተ ከአስር ዓመት በላይ የሆነ ሲሆን፣ ቡድኑ  በጎረቤት ሃገራትና በአባይ ተፋሰስ ሃገራት የሥራ ጉብኝቶችን በማድረግ ኢትዮጵያ እና በሃገራቱ ህዝቦች መካከል የህዝብ ለህዝብ ትስስር እንዲጎለብት የበኩሉን ጥረት ሲያደርግ መቆየቱ ይታወሳል።

 

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.