Fana: At a Speed of Life!

ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ የአብሮነት፣ የስኬት፣ የፍቅርና የቱሪስት መስህብ በመሆን የአገራችንን ገጽታ ገንብቷል – ም/ ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ

አዲስ አበባ፣ ጥር 2፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ከሩጫና ከስፖርትነት ባለፈ የአብሮነት፣ የስኬት፣ የፍቅር እንዲሁም የቱሪስት መስህብ በመሆን የኢትዮጵያን ገጽታ መገንባቱን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ገለጹ።
20ኛውን ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያን ያስጀመሩት ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች እንዳሉት÷ እንደወትሮዉ ሁሉ በድምቀት፣ አዝናኝ እና አስደሳች በሆነ መልክ በከተማችን እየተካሄደ ይገኛል።
እኛም እንደሩጫው ሁሉ አገራችን በምታደርገው ድህነትን የማሸነፍ፣ ዘላቂ እድገትን የማስመዝገብ እና የታላቅነት ጉዞ በየእለት ኑሮአችን አሸናፊዎች እንሁን ሲሉ መልዕክት ማስተላለፋቸውን ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፕሬስ ሴክሬታሪ ያገኘነው መረጃ አመልክቷል።
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.