Fana: At a Speed of Life!

የ2013 ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ጥር 2፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) የ2013 ታላቁ ሩጫ ሁሉንም የኮቪድ 19 ፕሮቶኮል እና መከላከያ መንገዶች ተከትሎ መካሄዱ ተገልጿል።
ውድድሩ መነሻውን መስቀል አደባባይ ያደረገ ሲሆን መድረሻው ደግሞ አትላስ አካባቢ መሆኑ ታውቋል፡፡
በውድድሩ ከጤና ሯጮች በተጨማሪ 300 የሚሆኑ ወንድ እና ሴት አትሌቶች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡
በዚህም በሴቶች ፅጌ ገብረ ሰላማ ከኢትዮ አትሌትክስ ውድድሩን በቀዳሚነት ስታጠናቅቅ ሁለተኛ ደረጃን በመያዝ ያጠናቀቀችው ደግሞ መድን ገብረ ስላሴ ከንግድ ባንክ ናት፤ ገበያነሽ አያሌው ከመከላከያ ውድድሩን በሶስተኝነት አጠናቃለች።
እንዲሁም በወንዶች በተደረገ ውድድር አቤ ጋሻሁን ከአማራ ማረሚያ ውድድሩን በአንደኝነት ሲያጠናቅቅ ታደሰ ወርቁ ከደቡብ ፓሊስ ሁለተኛ ደረጃን በመያዝ እንዲሁም ሚልኬሳ መንገሻ ከሰበታ ክለብ ውድድሩን በሶስተኝነት አጠናቀዋል፡፡
አሸናፊ ለሆኑ አትሌቶች የታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ መስራች እና የቦርድ ሊቀመንበር ሻለቃ አትሌት ኃይሌ ገብረስላሴ ፣የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌደሬሽን ፅህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ቢልልኝ መቆያ እና የቶታል ስፔሻሊስት እና የ ቢ ቱ ቢ ቢዝነስ ማኔጀር አቶ በኩረፅዮን ወልደእየሱስ ሽልማት አበርክተዋል፡፡
ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ዘንድሮ 20ኛ ዓመቱ ላይ የደረሰ ሲሆን በኢትዮጵያ በ20 አመት ቆይታው ከ500ሺህ በላይ ተሳታፊዎችን ማስተናገዱ ታውቋል፡፡
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.