የሀገር ውስጥ ዜና

ምህረት የህክምና አቅርቦት የተሰኘ ድርጅት 290 ሺህ ዶላር የሚያወጡ መድሃኒቶችና የህክምና ቁሳቁሶችን ድጋፍ አደረገ

By Tibebu Kebede

January 11, 2021

አዲስ አበባ ፣ ጥር 3 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)ምህረት የህክምና አቅርቦት የተሰኘ ድርጅት 290 ሺህ 281 ዶላር የሚያወጡ የህክምና ቁሳቁሶችን ድጋፍ ማድረጉን በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር ፍፁም አረጋ አስታወቁ።

ድርጅቱ መድሃኒቶችና የግል የህክምና ቁሳቁሶችን ድጋፍ ማድረጉን ነው አምባሳደሩ የገለፁት።

የተደረገው የመድሃኒት እና የህክምና ቁሳቁስ ድጋፍ በኢትዮጵያ ለሚገኙ ታካሚዎች እና የህክምና ባለሙያዎች ጥቅም ላይ እንደሚውል ተገልጿል።

ምህረት የህክምና አቅርቦት የተሰኘው ለትርፍ ያልተቋቋመው ይህ ድርጅት በደሃ ሀገራት ለሚገኙ ዜጎች ካደጉ ሀገራት የተትረፈረፉ የህክምና አቅርቦቶችን እና ቁሳቁሶችን በማሰባሰብና በመጠገን የሚያሰራጭ ነው።