Fana: At a Speed of Life!

በአማራ ክልል ለተፈናቀሉና በተፈጥሮ አደጋ ምክንያት ለተጎዱ ዜጎች 413 ሺህ ኩንታል የምግብ እህል በየወሩ ድጋፍ እየተደረገ መሆኑ ተገለፀ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 3 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በአማራ ክልል ለተፈናቀሉና በተፈጥሮ አደጋ ምክንያት ለተጎዱ 3ሚሊየን ዜጎች 413 ሺህ ኩንታል የምግብ እህል በየወሩ ድጋፍ እየተደረገ መሆኑን የክልሉ የአደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ፕሮግራምልዩ ድጋፍ የሚሹ አካባቢዎች ማስተባበሪያ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡
ኮሚሽነሩ ዘላለም ልጃለም እንደገለፁት÷ በቤኒሻንጉል፣ በኦሮሚያ፣በደቡብና ትግራይ ክልሎች ከ2010 ዓ.ም ጀምሮ 271 ሺህ የሚሆኑ ዜጎች መፈናቀላቸውን ተናግረዋል፡፡
ከዚህ ውስጥም ከ2013 ዓ.ም በፊት 159 ሺህ ዜጎች በቤኒሻንጉል፣ በደቡብ ፣በኦሮሚያና በትግራይ ክልሎች መፈናቀላቸውን ገልፀዋል፡፡
ከ98ሺህ በላይ ዜጎች የተፈናቁሉት ደግም በቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል መሆኑን ኮሚሽነር ዘላለም አስረድተዋል፡፡
በቤኒሻንጉል ለተፈናቀሉት ዜጎች 10 ሺህ ኩንታል የምግብ እህል ድጋፍ መደረጉን ነው ኮሚሽነሩ የተናገሩት ፡፡
በአጠቃላይም የክልሉ የአደጋ መከላከልና ምግብ ዋሰትና ማስተባበሪያ ኮሚሽን 1 ነጥብ 8 ሚሊየን የልማታዊ ሴፍቲኔት ተቃሚዎች ፣በተፈጥሮ አደጋ ተጎጂ ለሆኑ 781 ሺህ ዜጎች እና 271 ሺህ ተፈናቃዮች በየወሩ 413 ሺህ ኩንታል የምግብ እህል ድጋፍ እያደረገ መሆኑን ኮሚሽነር ዘላለም ገልፀዋል፡፡
በናትናኤል ጥጋቡ
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.