Fana: At a Speed of Life!

የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመግታት ለስድስት ወራት የሚቆይ ንቅናቄ ተጀመረ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 3 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኮሮና ቫይረሰን ስርጭት ለመግታት ለስድስት ወራት የሚቆየው ንቅናቄ ዛሬ ጀምሯል።
ንቅናቄው በመዘናጋት ምክንያት ወደ ከፍተኛ ሀገራዊ አደጋ እየተሸጋገረ ያለውን የኮሮና ቫይረስ ስርጭት መግታትን አላማ ያደረገ መሆኑን የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።
በኢትዮጵያ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ከሚመረመሩ ዜጎች ውስጥ በኮቪድ 19 የሚያዙ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ መምጣቱ በቫይረሱ ከተያዙት ውስጥ ደግሞ ለከፍተኛ ህመም የሚጋለጡት መጨመራቸው እና የመተላለፍ መጠኑ ከፍተኛ የሆነው የኮቪድ 19 ዝርያ ንቅናቄውን ለማስጀመር ምክንያት ናቸው ተብሏል።
በመሆኑም የቫይረሱን ስርጭት ለመግታት በቀጣይ ስድስት ወራት የሚሰሩ ስራዎችም ይፋ ተደርገዋል።
በዚህም የህዝቡን ንቃት የማሳደግ ስራ በልዩ ትኩረት ይሰራል ተብሏል።
30 ሚሊየን ጭምብል አቅም ለሌላቸው ማከፋፈል፣ ጭምብል ላላደረገ ዜጋ አገልግሎት ያለመስጠት እና በተማሪዎች የሚከወን የቅስቀሳ እና የግንዛቤ ማስጨበጫ ፕሮግራሞች ተጠቃሽ ናቸው።
በተጨማሪም ኮቪድ 19 ለመከላከል የወጣውን መመሪያ 30 /2013 ተግባራዊ እንዲደረግ የክትትል እና የቁጥጥር ስራ ይሰራል ተብሏል።
በብስራት መለሰ
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.