Fana: At a Speed of Life!

በመኸር እርሻ ከለማው ሠብል በዘጠኝ ሚሊየን ሄክታር ላይ የነበረው ተሰብስቧል-ግብርና ሚኒስቴር

አዲስ አበባ ፣ ጥር 3 ፣2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ ባለፈው መኸር በ13 ነጥብ 4 ሚሊየን ሄክታር መሬት ከለማው ሠብል በዘጠኝ ሚሊየን ሄክታር ላይ የነበረው መሰብሰቡን የግብርና ሚኒስቴር አስታወቀ።
በሚኒስቴሩ የሠብል ልማት ዳይሬክተር አቶ ኢሳያስ ለማ ÷ በ2012/2013 የመኸር እርሻ በተለያዩ የሃገሪቱ አካባቢዎች 13 ነጥብ 4 ሚሊየን ሄክታር መሬት በሰብል ተሸፍኗል ብለዋል።
ከዚሁ ውስጥ በዘጠኝ ሚሊየን ሄክታር ላይ የነበረው ሠብል መሰብሰቡን የገለጹት ዳይሬክተሩ÷ በትግራይ ክልል ምርት ቢሰበሰብም የተቀናጀ መረጃ ባለመኖሩ በአሃዙ አልተካተተም ብለዋል።
በመኸር እርሻ ከዕቅድ በላይ መታረሱን ገልጸው በሃገሪቱ አብዛኛው ምርት መሰብሰቡንና የቀረው ከ15 በመቶ በታች መሆኑን ተናግረዋል።
ከ16 ሚሊየን ኩንታል በላይ የአፈር ማዳበሪያ ተዘጋጅቶ እንደነበርም ነው የገለጹት።
በዚህም 80 በመቶው ጥቅም ላይ መዋሉንና ቀሪው ለመስኖና ለበልግ እርሻ እንደሚውል ጠቁመዋል።
ለመኸር እርሻ ከ700 ሺህ ኩንታል በላይ ምርጥ ዘር ለአርሶ አደሮች መቅረቡንና እንደ አፈሩ ተስማሚነት ከአምስት አይነት በላይ የአፈር ማዳበሪያ ጥቅም ላይ መዋሉንም አንስተዋል።
እንደ ዳይሬክተሩ ገለጻ ኮሮናቫይረስ፣ የጎርፍ አደጋና የአንበጣ መንጋ በሠብል ምርት ላይ በቤተሰብ ደረጃ የተወሰነ ተጽዕኖ ቢያስከትልም በሃገር ደረጃ ለማግኘት በታቀደው ምርት ላይ ተጽዕኖ አላሳደረም።
ከበቂ በላይ ዝናብ መጣሉ፣ ለአርሶ አደሮች የሚፈለገው ስልጠናና ግብዓት በወቅቱ መሰጠቱ ከሚፈለገው በላይ ምርት ለማግኘት አስችሏልም ነው ያሉት ።
ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ እንዲቻል ከ3 ሚሊየን ሄክታር በላይ መሬት በሃገር አቀፍ ደረጃ በኩታ ገጠም እርሻ እንዲለማ ተደርጓል ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.