የሀገር ውስጥ ዜና

በምዕራብ ወለጋ ዞን በሁለት ወራት ውስጥ 265 የኦነግ ሸኔ አባላት ላይ እርምጃ መወሰዱን ፖሊስ ገለፀ

By Tibebu Kebede

January 11, 2021

አዲስ አበባ ፣ ጥር 3 ፣2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በምዕራብ ወለጋ ዞን በሁለት ወራት ውስጥ 265 የኦነግ ሸኔ አባላት ላይ እርምጃ መወሰዱን ፖሊስ ገለፀ፡፡

ሰሞኑን በዞኑ የህግ የበላይነትን ለማስከበር በተወሰደ እርምጃ 8 የኦነግ ሸኔ አባላት መደምሰሳቸውን የምዕራብ ወለጋ ዞን ፖሊስ መምሪያ አስታውቋል፡፡

ፖሊስ መምሪያው እንዳስታወቀው 6 የኦነግ ሸኔ አባላት እና 87 ግብረ አበሮቻቸው በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡

በሁለት ወራት በዞኑ ውስጥ በተሰራው የህግ የበላይነትን በማስከበር ስራው 265 የቡድኑ አባላት ላይ እርምጃ መወሰዱንም ነው ፖሊስ ያስታወቀው፡፡

የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን እንደገለፀው በወቅቱ የተለያዩ የጦር መሳሪያዎችም ለመንግስት ገቢ ተደርገዋል፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤ ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!