የሀገር ውስጥ ዜና

በአካባቢ ዲፕሎማሲ ላይ ትኩረቱን ያደረገ አውደ ጥናት መካሄድ ጀመረ

By Tibebu Kebede

January 11, 2021

አዲስ አበባ ፣ ጥር 3 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በአካባቢ ዲፕሎማሲ ላይ ትኩረቱን ያደረገ አውደ ጥናት መካሄድ ጀመረ፡፡

በአውደ ጥናቱ አምባሳደሮች እና ዲፕሎማቶች ተሳታፊ ሲሆኑ በአየር ንብረት ለውጥ ሳይንስና የአየር ንብረት ዲፕሎማሲ፣ ዓለም አቀፍ የአየር ንብረት ለውጥ ፖሊሲ ማዕቀፍ እና ድርድሮች ላይ ትኩረቱን ያደርጋል ተብሏል፡፡

በአየር ንብረት ለውጥ ላይ ያሉ ዓለም አቀፍ እሳቤዎችም የአውደ ጥናቱ የትኩረት አቅጣጫዎች መሆናቸውንከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዲኤታ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን አውደ ጥናቱ ኢትዮጵያ በዓለም አቀፉ መድረክ በአየር ንብረት ለውጥ ላይ ያላትን ቁርጠኛ አቋም ለማሳየት ያለመ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በአፍሪካ ቀንድ የተከሰተውን ድርቅ፣ የጎርፍ አደጋ እና የአንበጣ መንጋ ያነሱት አምባሳደር ሬድዋን፥ ለአየር ንብረት ዲፕሎማሲ ትኩረት መስጠት አስፈላጊ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡

አውደ ጥናቱ ለቀጣዮቹ አራት ቀናት የሚቆይ ይሆናል፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤ ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!