Fana: At a Speed of Life!

አምባሳደር አብዱልፈታህ ከኩዌት የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 3 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በኩዌት የኢትጵያ ልዩ መልዕክተኛና ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር አብዱልፈታህ አብዱላሂ ከኩዌቱ የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር አብዱልሐሚድ አል-ፈይለካዊ ጋር የሁለቱን ሃገራት ግንኙነት በሚያጠናክሩ ጉዳዮችና በወቅታዊ ሃገራዊ ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል።

በውይይቱ በሁለቱ ሃገራት መካከል የጋራ ትብብሮችን ለማጠናከር በሚያስችሉ መንገዶች ላይ መክረዋል፡፡

እንዲሁም በሁለቱ ሃገራት መካከል ይካሄዳል ተብሎ በታቀደው የሚኒስትሮች የጋራ ኮሚሽን ስብሰባ እና በሃገራቱ መካከል በረቂቅ ደረጃ የሚገኘውን የሰራተኞች ስምሪት ስምምነት በተፋጠነ መልኩ መቋጨት በሚቻልባቸው መንገዶች ላይ መክረዋል።

በተጨማሪም አምባሳደር አብዱልፈታህ የኢትዮጵያ መንግሥት በትግራይ ክልል ያካሄደውን ሕግን የማስከበርና የህልውና ዘመቻ አስመልክቶ ለረዳት ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

ረዳት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ በበኩላቸው የኢትዮጵያ መንግሥት በትግራይ ክልል ያካሄደው ዘመቻ ጥበብ የተሞላበትና ማንኛውም ኃላፊነት የሚሰማው መሪ ሊያደርገው የሚገባ ተግባር መሆኑን ገልጸው÷ በዚህ ስኬት ደስተኛ መሆናቸውን ከኩዌት የኢትዮጵያ ኤምባሲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.