Fana: At a Speed of Life!

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል 6ኛውን ሀገራዊ ምርጫ በሠላማዊ መንገድ ለማካሄድ ክልል አቀፍ የሠላምና ደህንነት ምክር ቤት ተቋቋመ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 3 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ ) በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል 6ኛውን ሀገራዊ ምርጫ በሠላማዊ መንገድ ለማካሄድ የሚያስችል ክልል አቀፍ የሠላምና ደህንነት ምክር ቤት ተቋቋመ፡፡
ክልል አቀፍ የሠላምና ደህንነት ምክር ቤቱ 6ኛው ሀገራዊ ምርጫ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በህዝቡ ዘንድ ተዓማኒነትን ያገኘ፣ ነፃ፣ ግልፅ፣ ፍትሃዊ እንዲሆን ከመሥራት ባሻገር በሠላማዊ እና ዴሞክራሲያዊነትን በተላበሰ መልኩ እንዲጠናቀቅ የሚሠራ መሆኑ ተገልጿል።
የክልሉ ርዕሰ-መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሀሠንን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች፣ የዞን፣ የማኦና ኮሞ ልዩ ወረዳን ጨምሮ የወረዳና የከተማ አስተዳደር አመራሮችና የፀጥታ አካላት የተሳተፉበት የውይይት መድረክ ተካሂዷል።
የክልሉ ጠቅላይ ዓቃቤ ህግ አቶ ሰይድ ባበክር÷ ምርጫው ፍትሃዊ በሆነ መልኩ እንዲጠናቀቅ ከምክር ቤቱ ባሻገር ሁሉም የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ ጥሪ አቅርበዋል።
የክልሉ ርዕሰ-መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሀሠን በበኩላቸው÷ 6ኛው ሀገራዊና ክልላዊ ምርጫ እንደ ሀገር በተቀመጠው የጊዜ ሰሌዳ መሠረት ለማስኬድ በገዢው ፓርቲና መንግሥት በኩል ጥረት ቢደረግም በተለያዩ ምክንያቶች ምርጫውን ማስኬድ ሳይቻል መቅረቱን አስታውሰዋል፡፡
ርዕሰ መስተደድሩ አያያዘውም ምርጫው በህዝቡ ዘንድ ተዓማኒነት ያተረፈ፣ ነፃ፣ ግልፅ፣ ፍትሃዊ፣ ሠላማዊና ዴሞክራሲያዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ የተዋቀረው ክልል አቀፍ የሠላምና የደህንነት ምክር ቤት ኃላፊነቱን እንዲወጣ ጥሪ አቅርበዋል።
የመድረኩ ተሳታፊዎች በበከላቸው÷ ምርጫው ሠላማዊና ዴሞክራሲያዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ የሚጠበቅባቸውን ኃላፊነት እንደሚወጡ ገልጸዋል።
ከዚሁ ጎን ለጎን በመተከል ዞን የተከሰተውን የፀጥታ ችግር በዘላቂነት ለመፍታት በቅርቡ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የተቋቋመው ግብረ-ኃይል የጀመረውን የህግ ማስከበር ተግባር በመደገፍና ቀጠናውን ወደ ነበረበት ሠላም በመመለስ 6ኛውን ሃገራዊና ክልላዊ ምርጫ ለማስኬድ የሚያስችሉ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች መጀመራቸው ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታ፡፡
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.