Fana: At a Speed of Life!

ቦርዱ የምርጫ ጉዳዮችን የሚመለከቱ ችሎቶች ምሥረታ ሂደትን በተመለከተ ከፍርድ ቤቶች ፕሬዚዳንቶች ጋር ተወያየ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 3 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የምርጫ ጉዳዮችን የሚመለከቱ ችሎቶች ምሥረታ ሂደት ያለበትን ደረጃና በዚህ ረገድ ከባለድርሻ አካላት የሚጠበቁ የተለያዩ ሚና እና ኃላፊነቶች ላይ ከፍርድ ቤቶች ፕሬዘዳንቶች ጋር ውይይት አደረገ።

የቦርዱ ምክትል ሰብሳቢ  አቶ ውብሸት አየለና የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ምክትል ፕሬዚዳንት  አቶ ሰለሞን አረዳ በተገኙበት ከክልል ፍርድ ቤቶች ፕሬዚዳንቶችና ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ጋር ነው ውይይቱ የተካሄደው።

አቶ ውብሸት የቦርዱንና የፍርድ ቤቶችን የጋራና የተናጠል ኃላፊነቶች ለያይቶ ማየቱ እንዲሁም የቦርዱን የሥልጣን ኃላፊነት ወሠኑን መረዳት አስፈላጊ መሆኑን አስረድተዋል።

አቶ ሰለሞን አረዳ በበኩላቸው ምርጫ የሕግ የበላይነት መኖሩን ማረጋገጫ መሆኑን ገልጸው፤ የምርጫን ቅቡልነት ማረጋገጥ የሚቻለው የምርጫውን ፍትሐዊነት ማረጋገጥ ሲቻል ነው ሲሉ አጽንኦት ሰጥተዋል።

የክልል ፍርድ ቤቶች ፕሬዚዳንቶች የመድረኩን መዘጋጀት አመስግነው በቀጣይም የተለያዩ ተመሳሳይ መድረኮች መኖር እንዳለባቸው ገልጸዋል።

ፕሬዚዳንቶቹ በዋነኛነት አሉብን ያሏቸውን የሎጀስቲክና የሃብት እጥረቶች የገለፁ ሲሆን፤ የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ምክትል ፕሬዚዳንት  አቶ ሰለሞን አረዳ ያሉባቸውን ችግሮች መናገራቸው እየተናበቡ ችግሮችን ለመፍታት የሚደረገውን ጥረት እንደሚረዳ ገልፀዋል።

በትብብር ችግሮቹን ለመፍታት ጥረት እንደሚደረግም ተናግረዋል።

አቶ ሰለሞን በውድድር መሀል አለመግባባቶች እንደሚኖሩ ጠቅሰው በተፎካካሪ ፓርቲዎችም መሃል በሚደረገው ውድድር ሊፈጠሩ የሚችሉት አለመግባባቶችም ከዚህ ተለይተው እንደማይታዮና ዋናው ነገር አለመግባባቶች ሲፈጠሩ ቀልጣፋና ውጤታማ ውሣኔዎችን ለመስጠት የሚያስችሉ በቂ ዝግጅቶች ማድረግ መቻል ነው ሲሉ አብራርተዋል።

ግንቦት ላይ ለሚደረግ ምርጫ ሊያጋጥሙ የሚችሉ ክርክሮች የግድ ግንቦት ላይ ብቻ ያጋጥማል ማለት እንዳልሆነና ከወዲሁ ዝግጅት አስፈላጊ መሆኑን መናገራቸውን ከቦርዱ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.