Fana: At a Speed of Life!

የገዳ ሥርዓት እሴቶች ለሀገር አንድነትና ወንድማማችነት ጠቀሜታቸው የጎላ ነው – የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር

አዲስ አበባ ፣ ጥር 3 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የገዳ ሥርዓት እሴቶች ለሀገር አንድነትና ወንድማማችነት ጠቀሜታቸው የጎላ በመሆኑ ተንከባክቦና ጠብቆ ለቀጣዩ ትውልድ ማስተላለፍ እንደሚገባ የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ጥሪ አቀረበ።

የገዳ ሥርዓት በተመድ የትምህርት፣ ሳይንስና ባህል ተቋም (ዩኔስኮ) የተመዘገበበት አራተኛ ዓመትን አስመልክቶ የጉጂ የገዳ አደረጃጀት ትርኢትና ባህላዊ ኪነጥበብ ዝግጅት በቡሌ ሆራ ከተማ ተካሄዷል።

በዝግጅቱ ላይ የተገኙት የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር ዲኤታ ወይዘሮ ፍርሃት መሐመድ እንዳሉት የሀገሪቱ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች የብዙሃን ባህልና እሴቶች ባለቤት ናቸው።

በተለይ የጉሚ ኢሬቻ የሴቶችን እኩልነት ያከበረው የሀደ ሲንቄ እንዲሁም የጉዲፈቻና መሰል ጠቃሚ እሴቶች መገለጫ የሆነው የገዳ ሥርዓት አካል መሆኑን ጠቅሰዋል።

የሥርዓቱ እሴቶች ለሀገር አንድነትና ወንድማማችነት ጠቀሜታቸው የጎላ በመሆኑ ተንከባክቦና ጠብቆ ለቀጣዩ ትውልድ ማስተላለፍ ይገባል ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

የገዳ ሥርዓት በዩኔስኮ ከተመዘገበ አራት ዓመታት ማስቆጠሩን ያስታወሱት ሚኒስትር ዲኤታዋ በክብረ በዓሉ የታየው የገዳ ትርኢት እሴቱን ለማስተላለፍ የሚደረገውን ጥረት ያጠናክረዋልመ ነው ያሉት።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.