የሀገር ውስጥ ዜና

ፖሊስ ለበዓሉ በቂ ዝግጅት ማድረጉን ገለፀ

By Tibebu Kebede

January 06, 2020

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 27፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የገና በዓል በሰላም እንዲከበር በቂ ዝግጅት ማድረጉን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል።

በኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነትና የሚዲያ ሀላፊ ዋና ኢንስፔክተር ማርቆስ ታደሰ ለጣቢያችን እንደተናገሩት፥ ፖሊስ ኮሚሽኑ ለበዓሉ በቂ ዝግጅት አድርጓል።

የፖሊስ አባላትም ሰዎች በሚበዙባቸው የግብይት ቦታዎች እና የትራፊክ ፍሰት በሚበዛባቸው አካባቢዎች ተሰማርተዋል ነው ያሉት።

በተለይም ስርቆት፣ ቅሚያ፣ ማታለል እና ባዕድ ነገር ከምግብ ጋር ቀላቅሎ መሸጥ በበዓል ግብይት ጊዜ ሊከሰቱ የሚችሉ ወንጀሎች በመሆናቸው ህብረተሰቡ ለግብይት ሲወጣ ጥንቃቄ እንዲያደርግ አሳስበዋል።

በጌታሰው የሺዋስ