የሀገር ውስጥ ዜና

የአጊቱ ጉደታ አስከሬን አዲስ አበባ ገባ

By Tibebu Kebede

January 12, 2021

አዲስ አበባ ፣ ጥር 4 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤን እና በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የመንግስት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት አስተባባሪ አቶ ጃንጥራር አባይን ጨምሮ ቤተሰቦቿ እና ሌሎች የመንግስት የስራ ኃላፊዎች ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በመገኘት አስከሬኑን ተቀብለዋል፡፡

በጣልያኗ ፍራሲሎንጎ ከተማ ፍየል እያረባች የፍየል ተዋጽኦዎችንና የቆዳ ቅባቶችን በመሸጥ የጠንካራ ሠራተኛነት ተምሳሌት የነበረችው አጊቱ ጉደታ በሰራተኛዋ ለህልፈት መዳረጓ መገለጹ ይታወሳል፡፡፡

ኢትጵያዊቷ አጊቱ ጉደታ በፈረንጆቹ 2010 ወደ ጣሊያን በስደት ማምራቷን መረጃዎች ያመላክታሉ፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤ ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!