Fana: At a Speed of Life!

አምባሳደር ትዝታ ለህንድ የንግድ ማህበረሰብ በኢትዮጵያ የኢንቨስትመንት አማራጮች ዙሪያ ማብራሪያ ሰጡ

አዲስ አበባ፣ ጥር 4፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በህንድ የኢትዮጵያ አምባሳደር ዶክተር ትዝታ ሙሉጌታ ለህንድ የንግድ ማህበረሰብ አባላት በኢትዮጵያ ሰላለው ምቹ የኢንቨስትመንት አማራጭ ማብራሪያ ሰጡ።

በህንድ የኤክስፖርት ድርጅት የተዘጋጀና ከኮቪድ 19 በኋላ በኢትዮጵያና ህንድ ያለው የንግድና ኢንቨስትመንት አማራጭ በሚል ርዕስ በበይነ መረብ ተካሄዷል።

በፎረሙ ላይ አምባሳደር ዶክተር ትዝታ፣ በኢትዮጵያ የህንድ አምባሳደር ሮበርት ሼትኪንቶንግ፣ የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ዋና ፀሃፊ የሱፍ አዴምኑር እና ከ120 በላይ የህንድ የንግዱ ማህበረሰብ አባላት ተሳታፊ ሆነዋል።

አምባሳደር ትዝታ በኢትዮጵያና ህንድ መካከል ስላለው ጠንካራ የንግድ ግንኙነት እና ለህንድ የንግድ ሰዎች በኢትዮጵያ ስላለው ምቹ የኢንቨስትመንት አማራጭ ገለፃ አድርገዋል።

ህንድ በኢትዮጵያ በቀጥታ የውጭ ኢንቨስትመንት መዕዋለ ነዋይ በማፍስስ ሶስተኛ ደረጃ ላይ እንደምትገኝ በመግለፅ ኢትዮጵያ ካላት ያልተነካ አቅም የህንድ ባለሃብቶች አሁንም ሌሎች አማራጮችን ሊመለከቱ እንደሚገባ ገልፀዋል።

ከኢትዮጵያ ወደ ህንድ እና በተቃራኒው የተለያዩ ምርቶችን ኤክስፖርት ማድረግ ላይ ስራዎችን መስራት እንደሚገባም አፅንኦት ሰጥተው ተናግረዋል።

በኢትዮጵያ የህንድ አምባሳደር ሮበርት ሼትኪንቶንግ በውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት የኢትዮጵያ መንግስት የህንድ ባለሀብቶችን ለመሳብ በከፍተኛ ሁኔታ እየተንቀሳቀሰ እንደሚገኝ ገልጸዋል።

በመሆኑም የህንድ ባለሀብቶች በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ፣ በግብርና ማቀነባበሪያ፣ በመድሃኒት ምርት፣ በቴሌኮም እና በሌሎች አቅም ባላቸው ዘርፎች እንዲሰማሩ አምባሳደሩ ጥሪ አቅርበዋል።

በኢትዮጵያ መዕዋለ ነዋያቸውን ያፈሰሱ ስኬታማ የህንድ ባለሀብቶች ኢትዮጵያ ስላላት ምቹ የንግድ ሁኔታ በተመለከተ በፎረሙ ላይ የተሳተፉ  ሌሎች የህንድ ባለሀብቶች ገለፃ ሰጥተዋል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.