Fana: At a Speed of Life!

የፖሊስ ኮሚሽነሮች ጉባዔ በፖሊስ ዘርፍ የ10 ዓመት ስትራቴጂክ ዕቅድ ላይ በመግባባት ተጠናቀ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 4 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በፖሊስ ኮሚሽነሮች ጉባዔ በፖሊስ ዘርፍ የ10 ዓመት ስትራቴጂክ ዕቅድ ላይ በመወያየት መግባባት ላይ ተደርሷል።

ለሁለት ቀናት በቢሾፍቱ የተካሄደው የፌደራል፣ የክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች ፖሊስ ኮሚሽነሮች 12ኛ የጋራ ጉባዔ ተጠናቋል።

በ10 ዓመቱ ስትራቴጂክ ዕቅድ ለወገን አለኝታ የሆነ፣ ዘመናዊ መሳሪያ የታጠቀና ጠንካራ ክህሎት ያለው የፖሊስ ሠራዊት እንደሚገነባ በተካሄደው ውይይት መግባባት ላይ ተደርሷል።

በተጨማሪም ስድስተኛው ሃገራዊ ምርጫ ያለአንዳች የፀጥታ ስጋት እንዲከናወንና ሕዝቡ የፈለገውን መምረጥ እንዲችል ፖሊስ የፀጥታ ማስከበሩን ስራ በትጋት እንደሚፈፅም ተገልጿል።

ለዚህ በተዘጋጀው የምርጫ ዕቅድ ላይ ውይይት ተደርጎ መግባባት ላይ የተደረሰ ሲሆን ክልሎችም የፌደራል ፖሊስ ያዘጋጀውን የምርጫ ዕቅድ አብነት በማድረግ የራሳቸውን አዘጋጅተው ወደተግባር ይገባሉ ተብሏል።

በትናንትናው የጉባዔው ውሎ የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጄኔራል ደመላሽ ገብረሚካኤል በሃገሪቷ የሠላምና የዴሞክራሲ ግንባታ ጠንካራ ሆኖ እንዲቀጥል ፖሊስ ከመቼውም ጊዜ በበለጠ ዝግጁ መሆኑን አረጋግጠዋል።

ጎን ለጎንም የሕግ የበላይነትን ለማረጋገጥ ፖሊስ ሥራውን እንደሚያጠናክር ተናግረዋል።

ዘላቂ ሠላም እንዲረጋገጥ የሃገሪቷን ፖሊስ ወደተሻለ ደረጃ ለማሳደግ እንደሚሰራና በቀጣይ ፖሊስ በብሔር ሳይወሰን ለሁሉም የሰው ልጆች ክብር የሚያገለግልበት ሁኔታ እንደሚመቻችም ነው የተናገሩት።

በጉባዔው የፌደራል፣ የሁሉም ክልሎችና የሁለቱ ከተማ አስተዳደሮች ፖሊስ ኮሚሽነሮች መሳተፋቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.