Fana: At a Speed of Life!

የሴቶችን እና የእናቶችን ጤና ለማሻሻል ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ ነው- ዶ/ር ሊያ ታደሰ

አዲስ አበባ ፣ጥር 4 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በደም መፍሰስ ምክንያት እናት ለምን ትሙት በሚል መሪ ቃል የጤናማ እናትነት ወር ዛሬ መከበር ጀምሯል ።
በኢትዮጵያ ለአስራ አምስተኛ ጊዜ የሚከበረው ጤናማ የእናትነት ወር እስከ ጥር መጨረሻ ድረስ እንደሚከበር ተገልጿል።
በማስጀመሪያ መርሃ ግብሩ ላይ የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰን ጨምሮ ሴት ሚኒስትሮች እና ሌሎች ሀላፊዎች ተገኝተዋል፡፡
የጤና ሚኒስትር ሊያ ታደሰ የሴቶችን እና የእናቶችን ጤና ለማሻሻል ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል።
ከ10 ዓመት በፊት 10 በመቶ የሚሆኑ እናቶች ወደጤና ተቋማት የመሄድ ልማድ የነበራቸው ሲሆን፥ አሁን ላይ 51 በመቶ የሚሆኑ እናቶች ወደ ጤና ተቋማት እንደሚሄዱ ተነስቷል።
ይሁን እንጅ አሁንም ቢሆን ከእርግዝና እና ከወሊድ ጋር ተያይዞ በርካታ እናቶች ህይወታቸውን የሚያጡ ሲሆን÷ የእናቶችን ሞት ለመቀነስ ሁሉም ባለድርሻ አካላት ሊረባረቡ ይገባል ተብሏል።
በቅድስት ብርሃኑ
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.