Fana: At a Speed of Life!

ያገባኛል የተሰኘው ፕሮግራም በሀገሪቱን የጤና አገልግሎት ሁለንተናዊ ለውጥ እንደሚያመጣ ተገለፀ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 4 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የጤና ሚኒስቴር በሀያ አራት ሆስፒታሎች የጀመረው ያገባኛል (አይ ኬር) የተሰኘው ፕሮግራም በደብረ ብርሀን ኮምፕሪሄንሲቪ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የማስጀመሪያ መርሀግብር ተከናውኗል።
በመርሀ ግብሩ የተገኙት የጤና ሚኒስትር ዲኤታ ዶክተር ደረጀ ዱጉማ እንደተናገሩት አይኬር ሁሉን አቀፍ ለውጥ በሆስፒታሎች ለማምጣት፣ ሩህሩህ፣ የህመምተኞች ስቃይን የሚረዱ እና ሙያዊ ሀላፊነታቸውን በአግባቡ የሚወጡ ባለሙያዎችን ከማፍራትና፣ በሆስፒታሎች አገልግሎት ዙሪያ የማያሰሩ ስርአቶችን ለመፈተሽና በየሚያሰሩ አሰራሮች ለመዘርጋት እና አጋር አካላትን ለማሳተፍ የተቀረጸ መሆኑን ተናግረዋል።
በሀያ አራት ሆስፒታሎች በሙከራ ደረጃ መተግበር መጀመሩን የተናገሩት ሚኒስትር ዲኤታው በሂደት በሁለም የህክምና ተቋማት እንደሚተገበርም አስታውቀዋል።
የደብረ ብርሀን ኮምፕሪሄንሲቨ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታልም ትግበራውን መጀመሩን እና እያሳየ ያለው ለውጥም የሚበረታታ መሆኑን ገልጸው የጤና ሚኒስቴር 50 በመቶ፣ የክልል ጤና ቢሮ 30 በመቶና ሆስፒታሎች 20 በመቶ የተቀመጠላቸውን የበጀት ድርሻም ለፕሮግራሙ ተግባራዊነት እንደሚሸፍኑ መናገራቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
የአይ ኬር ኢኒሼቲቭ ማስጀመሪያ ፕሮግራም ላይ የተገኙ የአካባቢው ነዋሪዎችን በሰጡት አስተያየት የደብረ ብርሀን ኮምፕሪሄንሲቪ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ባለበት የቦታ ጥበት፣ የመድሀኒት እና የህክምና መሳሪያዎች እጥረት ምክንያት አዲስ አበባ ለህክምና ለመሄድ እንደሚገደዱ ተናግረው የሆስፒታል ማስፋፊያ ስራው በቂ እንዳልሆነ ሌሎች ግብአቶች እንዲሟሉ ጠይቀዋል።
የአማራ ክልል ጤና ቢሮ ሀላፊ ዶክተር መልካሙ አብተው ከህብረተሰቡ የሚነሱ ጥያቄዎች ትክክል እንደሆኑ ገልጸው የክልሉ ጤና ቢሮ ያገባኛል የተሰኘውን ፕሮግራም በመተግበር እና እስከ ታችኛው መዋቅር ያለውን አካል በማስተባበር ችግሩን ለመቅረፍ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.