Fana: At a Speed of Life!

የየካ ክፍለ ከተማ በህገ-ወጥ መንገድ በተገነቡ እና በተወረሩ መሬቶች ላይ እርምጃ መውሰድ ጀመረ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 4 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በህገ-ወጥ መንገድ በተገነቡ እና በተወረሩ መሬቶች ላይ እርምጃ መውሰድ መጀመሩን የየካ ክፍለ ከተማ አስታወቀ፡፡

የክፍለ ከተማው አስተዳደር በህገወጥ መንገድ ግንባታ የተካሄደባቸው ላይ ከህብረተሰቡ እና ከፀጥታ አካላት ጋር በመተባበር እርምጃ መውሰድ መጀመሩን አስታውቋል፡፡

የክፍለ ከተማው ደንብ ማስከበር ባለሙያዎች ከፀጥታ አካላት እና ከህብረተሰቡ ጋር በመሆን በህገ-ወጥ መንገድ የተወረሩ እና ግንባታ የተካሄደባቸው ቤቶች ላይ በሚወሰደው እርምጃ ህብረተሰቡ እያደረገ ያለውን ድጋፍ አጠናክሮ እንዲቀጥልም ጥሪውን አቅርቧል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከ1997 ዓ.ም ወዲህ በህገ-ወጥ መንገድ የተወረሩ መሬቶች እና ግንባታዎች ላይ በቅርቡ ጥናት ማካሄዱን ከአዲስ አበባ ከተማ ፕሬስ ሴክሬታሪያት ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.