የሀገር ውስጥ ዜና

የሀገር ፍቅር ቴአትር ቤት የእድሳት ሥራ ተጀመረ

By Tibebu Kebede

January 12, 2021

አዲስ አበባ፣ ጥር 4 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የሀገር ፍቅር ቴአትር ቤት የእድሳት ሥራ በዛሬው እለት ተጀመረ።

እድሳቱ ደረጃውን የጠበቀ አገልግሎት እንዲሰጥ ተደርጎ የሚከናወን መሆኑንም የአዲስ አበባ ባህል፣ ኪነጥበብና ቱሪዝም ቢሮ አስታውቋል።

“ሀገር በሀገር ፍቅር ይታደሳል ” በሚል መሪ ሃሳብ የእድሳት ማስጀመሪያ መርሃ ግብር ዛሬ ተከናውኗል።

በሥነ-ሥርዓቱ ላይ የተገኙት በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የከተማ አስተዳደሩ የአገልግሎት ሰጪ ተቋማት አስተባባሪ አቶ ዣንጥራር ዓባይ ቅርሶችን ማደስ ጥንቃቄ የሚጠይቅ ስራ መሆኑን ተናግረዋል።

ከዚህ አንጻርም ቢሮው በስራው የሚሳተፉ አካላት በቅንጅት እንዲሰሩ ጥሪ አቅርበዋል።

የከተማ አስተዳደሩ በእድሳቱ ላይ የሚጠበቅበትን ድጋፍ እንደሚያደርግ ማረጋገጣቸውን ከአዲስ አበባ ፕሬስ ሴክሬታሪያት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

የአዲስ አበባ ባህል፣ ኪነጥበብና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ ወይዘሮ ፋይዛ መሐመድ በኩላቸው ቴአትር ቤቱ ዘመን ተሻጋሪ አገልግሎት የሰጠና በሀገሪቱ በቀዳሚነቱ የሚጠቀስ መሆኑን አስታውሰዋል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤ ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!